| አሜሪካ በኤርትራ የጦር መሳሪያ... |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
|
አሜሪካ በኤርትራ የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ ላይ ማዕቀብ ጣለች
በጋዜጣው ሪፖርተር ዳይሬክቶሬት ኦፍ ዲፌንስ ትሬድ ኮንትሮልስ (ዲዲቲሲ) የተባለው የአሜሪካ ተቋም በኤርትራ የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ እንዳይካሄድ ማዕቀብ መጣሉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገለፀ፡፡ እርምጃው የአሜሪካ ዲፓርትመንት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የጦር መሳሪያ ኤክስፖርት ቁጥጥር አክት፣ 22 U.S.C. 2781 በ40 A ክፍል አሜሪካ በምታካሂደው የፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻ ኤርትራ በፍፁም ተባባሪ አለመሆኗን የተደረሰ ውሳኔ ቀጥተኛ ውጤት መሆኑ ታውቀዋል፡፡ ተቋሙ የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ ላይ እንዲህ ዓይነት ማዕቀብ ተግባራዊ የሚያደርግ በስቴት ዲፓርትመንቱ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ነው፡፡ የፌዴራል ሪጂስተር የጦር መሳሪያ ማዕቀቡን አስመልክቶ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት፣ ውሳኔው ተፈፃሚ የሚሆነው እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 ቀን 2008 ጀምሮ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ስቴት ዲፓርትመንቱ ኤርትራን በአሸባሪዎች ተርታ ለማስፈር ሲያስጠነቅቅ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያ የወጣው፣ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ኤርትራ በሶማሊያ ለሚገኙ ከአልቃኢዳ ጋር ትስስር ላላቸው ቡድኖች መሳሪያ ስታቀብል እንደነበር ካረጋገጠ በኋላ ነው፡፡ ስቴት ዲፓርትመንቱ ግን ኤርትራን ከአሸባሪ መንግሥታት ዝርዝር ውስጥ ከማስገባት እስከ አሁን ተቆጥቧል፡፡ ይሁንና ይህ የአሁኑ የማዕቀብ እርምጃ ለኤርትራ እምብዛም አስጊ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ ያሉት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ለኤርትራ የተደረገው ብዙም የጦር መሳሪያ ሽያጭ የለም፡፡ ማዕቀቡ ከሚያካትታቸው የጦር መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች መካከል፣ ለውጊያ የሚውሉ ሶፍትዌሮች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ሴንሰሮችና ሌዘር መሳሪያዎች፣ አቅጣጫ ጠቋሚ የበረራ መሳሪያዎችና የመሳሪያ መወናጨፊያዎች ይገኙበታል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |