| ይድረስ ለአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ኤጀንሲ |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
|
የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤቶች ኤጀንሲ ሰሞኑን ከ10ሺ በላይ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ዕጣ አውጥቷል፡፡ በዕጣውም መሠረት ይህን ያህል ቁጥር ያለው ቤት አልባ ነዋሪ የግል መኖሪያ ቤት ባለቤት ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ እጅግ የሚያስደስትና የሚያረካ ተግባር ይሆናል፡፡
ሆኖም ኤጀንሲው በሶስት ጉዳዮች ላይ አጽንኦት ሰጥቶ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር በማያጋልጥ መልኩ እንደገና ሊያየው ይገባል የምላቸውን ነጥቦች እጠቁማለሁ፡፡ አንደኛው ነጥብ ከቤት ተመዝጋቢዎች መካከል ጥቂት የማይባል ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች የራሳቸው መኖሪያ ቤት ያላቸውና ያለምንም ይሉኝታ ትርፍ ቤት ለመያዝ የሚንቀሳቀሱ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ ሁለተኛውና አሳሳቢው ጉዳይ ቤት ለማግኘት አንድ ቤተሰብ ባል፣ ሚስት፣ 18 ዓመት ያለፋቸው ልጆች የሚመዘገቡበት ሁኔታ መፈጠሩ ነው፡፡ በተለይ ባልና ሚስት በተለያየ ስም ሁለት ቤት ሊይዙ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ሶስተኛው ሴቶችን ለማበረታታት ሲባል የተሰጠው ፖለቲካዊ ውሣኔን ይመለከታል፡፡ በዕጣው ከተካተቱት 30 በመቶ ሴቶች ያዙ፡፡ እንደገና ከቀረው 70 በመቶ ውስጥ እኩል ይወዳደራሉ፡፡ በዚህ ስሌት ከተኬደ ሴቶች ከ60 በመቶ በላይ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ሴቶችን ለማበረታታት ሲባል ወንዶችን መበደል ወይም ፍትሐዊ ክፍፍልን ማዛባት ተገቢ አይደለምና እነዚህ ጉዳዮች ኤጀንሲው በሚገባ አጢኗቸው በቀጣይ መላ ቢያበጅላቸው ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ከማል፣ ከአዲስ አበባ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |