Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በ8 ወር ከ600 ሚሊዮን ብር...
በ8 ወር ከ600 ሚሊዮን ብር... E-mail
Wednesday, 08 October 2008
በ8 ወር ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ሲሚንቶ ገብቷል

በዳዊት ታዬ

በአገር ውስጥ የተፈጠረውን የሲሚንቶ እጥረት ለማቃለልና ያለውን ክፍተት ለማሟላት ሲሚንቶ ከውጭ እንዲገባ ከተደረገ ወዲህ በተለይ ባሳለፍነው አመት 8 ወራት ብቻ ከ625 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ሲሚንቶ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው እ.ኤ.አ በ2007 ስምንት ወራት ውስጥ 458.5 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚሆን ሲሚንቶ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል፡፡

ይህንን ያህል መጠን ያለው ሲሚንቶ ወደ አገር ውስጥ ገብቶ የማያውቅ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2006 ወቅት ወደ አገር ውስጥ ገብቶ የነበረው የሲሚንቶ መጠን 60.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ነው፡፡

ይህም አሃዝ የሚያመለክተው በ2007 በስምንት ወራት ከገባው ጋር ሲነፃፀር ከ395 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ እንዳለው ያሳያል፡፡

ወጪን በሚመለከት እ.ኤ.አ በ2006 ሙሉ ዓመት ለተገዛው ሲሚንቶ የወጣው ወጪ 68.6 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህም በ2007 አገሪቱ ለሲሚንቶ ግዥ የወጣው የገንዘብ መጠን ከ2006 ጋር ሲነጻጸር ከ575 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ማስመዝገቡን መረጃው ያሳያል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2006 በፊት ወደ አገር ውስጥ ይገባ የነበረው የሲሚንቶ ምርት አሁን እየገባ ካለው የሲሚንቶ መጠን ጋር የማይቀራረብ ነው፡፡

ቀደም ብሎ በነበረው የሲሚንቶ ግዥ እ.ኤ.አ በ2000 1943 ኪ.ግ፣ በ2002 387 ሺህ ኪ.ግ፣ በ2003 518.2 ሺህ ኪ.ግራም መግባቱን ያሳያል፡፡

በጥቅሉ ከ1997 እስ 2005 ድረስ አገሪቱ ለሲሚንቶ ግዥ በአማካይ ታወጣ የነበረው ወጪ ከሁለት ሚሊዮን ብር አይበልጥም፡፡
 
< Prev   Next >