Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ክረምት ወጣ፣ መፀው (አበባ) ገባ
ክረምት ወጣ፣ መፀው (አበባ) ገባ E-mail
Wednesday, 08 October 2008
Imageበሔኖክ ያሬድ

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ሲመጣ "አበባ አበባዬ መስከረም ጠባዬ" እየተባለ ይዘመራል፡፡ የዓመቱ ማብቂያ ጳጉሜን 5 ቀን አብቅቶ መስከረም 1 ቀን ሲመጣ የሚደረግለት አቀባበል  ነው፡፡ ሰኔ ውስጥ የገባው (በ25) ክረምት አብቅቶ ተከታዩ ወቅት (ክፍለ ዘመን) መፀው የሚገባው ወይም የሚብተው ግን ሁሌ መስከረም 26 ቀን ነው፡፡

መፀው አበባ ማለት ሲሆን ግሱ መፀወ፣ አበበ፣ አበባ ያዘ፣ አረገዘ፣ ደበደበ፣ ለማፍራትና ለመውለድ ለመዘርዘር በቃ ማለት እንደሆነ የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ይገልጻል፡፡

ምሥጢሩ መዐዛ መስጠት፣ እንቡጥና ፍሬ ማሳየት ነው፡፡ እስከ ታኅሣሥ 25 ቀን የሚዘልቀው መፀው፣ ወርኀ ጽጌ (የአበባ ወር"፣ ዘመነ ጽጌ (የአበባ ዘመን) ተብሎም ይታወቃል፡፡

ጽጌ፣ አበባ የፍሬ ምልክት፣ ውበት፣ ደም ግባት ያለው፣ ምድርንም በአበባ የሚያስጌጣት ነው፡፡ መስከረም 26 ቀን 2001 ዓ.ም የአበባ (መፀው) ወቅት ሲገባ ማለዳ ላይ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን (ሪፖርተር) በጽ/ቤቱ በልዩ አጋጣሚ አክብሮታል፡፡ ቢሮው በዕለቱ ከ"ሬንቦ ፍላወር" በተበረከተለት ሥነ ጽገያት (የተለያዩ የአበባ መልኮች) የአበባ መባቻን ዘክሮታል፡፡

የመፀው (አበባ) መባቻ በዓል ከዘመነ አክሱም በተለይ ከ4ኛው ምእት ዓመት ዠምሮ እስከ 15ኛ ምእት ድረስ መስከረም 26 ሲከበር ቆይቶ ወደ መስከረም 10 በመዘዋወር "ተቀጸል ጽጌ" (አበባን ተቀዳጅ) ተብሎ እስካሁን ሲከበር ቆይቷል፡፡

የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ (የበልግና ክረምት) በየጊዜው የሚሰጠውን ለመከርም (መፀው) የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልን እንጠብቅ፡፡
Last Updated ( Thursday, 09 October 2008 )
 
< Prev   Next >