| የማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ... |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
|
የማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ በገንዘብ እጥረት ችግር ገጥሞታል
ከሳምንታት በፊት ለቤጂንግ ኦሊምፒክ ጀግኖች የማዕረግና የማበረታቻ ሽልማት በግዮን ሆቴል ያበረከተው ፌዴራል ማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ የስፖርት ክለቡ በአሁኑ ሰዓት የገንዘብ እጥረት የክለቡን ሕልውና ክፉኛ እየተፈታተነው በመሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ሊታደጉት እንደሚገባ ኃላፊዎቹ አመልክተዋል፡፡ በግዮን ሆቴል የማዕረግና የማበረታቻ ሽልማት በተሰጠበት እለት የስፖርት ክለቡ በተለይ በአትሌቲክስ ተተኪዎችን ለማፍራት ቀርቶ፣ ያሉትን አትሌቶች እንኳ መጓጓዥና የላብ መተኪያ አሟልቶ ማቅረብ እየተሳነው እንደሚገኝ የክለቡ የበላይ ጠባቂ የሆኑት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ማዕረጉ ሀብተ ማርያም የተናገሩትን በመጥቀስ በአሁኑ ሰዓት በክለቡ የተጋረጠውን የገንዘብ እጥረት የገለፁት የክለቡ ኃላፊዎች አፋጣኝ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡ በተለያዩ የዓለምና የኦሊምፒክ አደባባይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረጉ ብርቅዬ አትሌቶች አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮማ፣ ጥሩነሽ ዲባባና ስለሺ ስህን የማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ያፈራቸው መሆኑን ያመለከተው ዜና "ክለቡን ማዳን የሁሉም ዜጋ ነው" ሲሉ ኃላፊዎቹ በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |