| "እያደር የሚጣፍጠው ወይን"... |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
|
ኃይሌ በርሊን ላይ በ2 ሰዓት 03 ደቂቃ 59 ሰከንድ በመግባት ማሸነፉንና ክብረ ወሰን መጨበጡን በአድናቆት ከዘገቡት መገናኛ ብዙሃን መካከል "የፍራንስ 24" ዘገባ የኃይሌን ገድል ስኬታማነት ከቆየ ወይን ጋር አነጻጽሮታል፡፡ "እያደር የሚጣፍጠው ወይን" በማለት፡፡ የ35 ዓመቱ ኃይሌ ዕድሜው ለሩጫ ቢገፋም ጣፋጭ ድልን እያጣጣመ መሆኑን አመልክቷል፡፡ የኃይሌ አዲሱ 26ኛው ክብረ ወሰን በታሪክ ከ2ሰዓት 04 ደቂቃ በታች የገባ የመጀመሪያው ሰው አድርጎታል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ኃይሌ በፖል ቴርጋት በ2 ሰዓት 04 ደቂቃ 55 ሰከንድ ተይዞ የነበረውንና ቴርጋት ከ2 ሰዓት 05 ደቂቃ በታች የገባ የመጀመሪያው አትሌት የተባለበትን ክብረ ወሰን፣ በ2ሰዓት 04 ደቂቃ 24 ሰከንድ በመፈጸም ክብሩን መጨበጡ ይታወሳል፡፡ ኃይሌ የበርሊን ማራቶንን ሦስት ጊዜ በማሸነፉም የመጀመሪያው ሰው ሆኗል፡፡ የማራቶንን ክብረ ወሰን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰበረው ኢትዮጵያዊ አበበ ቢቂላ ሲሆን፣ በ1957 ዓ.ም በቶኪዮ ኦሊምፒክ 2ሰዓት 12ደቂቃ በመፈፀም የዓለምና የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር የክብረ ወሰን ፋና ወጊ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁለተኛው ክብረ ወሰን በ1980 ዓ.ም ሮተርዳም (ሆላንድ) በ2 ሰዓት 06 ደቂቃ በመግባት ሰዓቱ በመስበር ያሸነፈው በላይነህ ዴንሳሞም ይታወሳል፡፡ |
|
| Last Updated ( Thursday, 09 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |