Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow ዴሞክራቶች የተሻለ ድምፅ...
ዴሞክራቶች የተሻለ ድምፅ... E-mail
Wednesday, 08 October 2008

Imageዴሞክራቶች የተሻለ ድምፅ እያገኙ መሆናቸውን ሪፖርቶች ገለፁ
በሀይሌ ሙሉ

የዴሞክራትና ሪፐብሊካን ፓርቲዎች በህዳር ወር በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚችሉ ሰዎች እንዲመዘገቡ ሲወተወቱ ከርመዋል፡፡ ሁለቱም ፓርቲዎች የድምፅ ሰጪዎቻቸውን ቁጥር ለመጨመር ታዋቂ ሰዎች የተሳተፉበትን የተለያዩ ዝግጅቶች አካሂደዋል፡፡ ባለፈው ወር ብቻ በተለያዩ ስቴቶች አራት ሚሊዮን የሚደርሱ አዲስ ድምፅ ሰጪዎች ተመዝግበዋል፡፡ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊዎች ናቸው፡፡

 

ዲሞክራቶች ትልቅ የፉክክር ቦታ ተደርጐ በሚወስደው ፍሎሪዳ ስቴት ከሪፐብሊካኖች በእጥፍ የሚበልጥ ድምፅ ሰጪ አግኝተዋል፡፡

በኮሎራዶ እና ኔቫዳ ስቴት ለምርጫ የተመዘገቡት አሜሪካኖች ድጋፍ በአማካይ ሲታይ ዲሞክራቶች 4 ለ 1 ይመራሉ፡፡ በሰሜን ካሮሊና ደግሞ ዴሞክራቶች 6 ለ 1 ይመራሉ፡፡

በቨርጂኒያ የመራጮች ምዝገባ በተካሄደበት ጊዜ መራጮች ለፓርቲዎች ያላቸው ድጋፍ በግልፅ ያልታየ ቢሆንም ዋሽንግተን ፖስት እንደገለፀው በርካታ ተመዝጋቢዎች የዴሞክራት ፓርቲ ታማኞች መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ በ2ዐዐ4 ባደረጉት ኘሬዚዳንታዊ ምርጫ ከላይ በተገለፁት አምስት ግዛቶች አሸናፊ የነበሩ ቢሆንም የዴሞክራት እጩ ሴናተር ባራክ ኦባማ ግን በግዛቶቹ ላይ ትኩረት ሰጥተው በመንቀሳቀሳቸው የአሁኑን ድጋፍ ለማግኘት ችለዋል፡፡

የኦባማ የምርጫ ዘመቻ ቡድን ድምፃዊ ብሩስ ስኘሪንግስቲንን በመያዝ በፔንስሊቫንያና በኦሀዩ ከክፍያ ነፃ የሆነ የሙዚቃ ዝግጅት በማካሄድ ተጨማሪ ድምፅ ሰጪዎች እንዲመዘገቡ አድርጓል፡፡

የሪፐብሊካኑ ተቀናቃኝ ጆን ማኬይን በበኩላቸው ሁለት የቀድሞ የአሜሪካ ፉትቦል ተጫዋቾችን ባለፈው ሳምንት ኦሀዩ በተካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ እንዲቀላቀሉአቸው ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡

ወጣቶች፣ ሂስፓኒኮች (የስፔን ዝርያ ያላቸው) እና አፍሪካ አሜሪካውያን በምርጫው እንዲሳተፉ ለማድረግ የዘመቻው አዘጋጆች ትኩረት ሰጥተው ተንቀሳቅሰውባቸዋል፡፡

አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ሴናተር ኦባማ እና ሄላሪ ክሊንተን የዴሞክራት ፓርቲን ወክለው በኘሬዚዳንትነት ለመወዳደር ያደረጉት ፉክክር ኦባማን ሳይጠቅማቸው አይቀርም፡፡ ይህንን ሲያስረዱም የዲሞክራት እጩ ኘሬዚዳንትን ለመምረጥ ከተመዘገቡት ሰዎች ይልቅ በአሁኑ ኘሬዚዳንታዊ ምርጫ የተመዘገቡ ድምጽ ሰጪዎች ብዙ መሆናቸውን እንደምክንያት ይወስዳሉ፡፡

ትናንት ማምሻው ላይ ክርክር ከመካሄዱ በፊት በእጩ ኘሬዚዳንቶቹ መካከል የቃላት ልውውጥ ተካሂዶ ነበር፡፡ ባራክ ኦባማ አሜሪካ ከፊቷ ለተጋረጠው የኢኮኖሚ ቀውስ ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ጆን ማኬይን የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱባቸው መሆኑን ኦባማ ተናግረዋል፡፡ ጆን ማኬን በበኩላቸው እርሳቸው ከአገር ውስጥ አበዳሪ ኢንዱስትሪዎች ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት ባራክ ኦባማ መዋሸታቸውን በመናገር፤ ተቀናቃኛቸው ቀደም ሲል በመንግሥት እንቅስቃሴ ውስጥ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ጠይቀዋል፡፡

በቅርቡ በተካሄደ የእለት ከእለት ምርጫ ቆጠራ ሴናተር ኦባማ ሀምሳ በመቶ ድምፅ ሲያገኙ ማኬን ደግሞ አርባ ሁለት በመቶ አግኝተዋል፡፡ አዲሱ የሲ.ኤን.ኤን ምርጫ ደግሞ ኦባማ አርባ አምስት ለሀምሳ ሦስት በመቶ እየተመሩ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ የዲሞክራት ፓርቲ እጩ ሚስተር ኦባማ ቁልፍ ድምፆችን እያገኙ ሲሆን የዋሽንግተን ፖስት ምርጫ ድምፅ ቆጠራም በኦሀዩ ሚስተር ሜኬንን ስድስት በመቶ ድምፅ ብልጫ እየመሩ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ ኦባማ አሸናፊ የሚሆኑ ከሆነ የኦሀዩ ስቴት በሪፐብሊካን ተመራጭ መያዝ እንደሚኖርበት ተጠቁሟል፡፡ ቆጠራው የኦባማ የምረጡኝ ቅስቀሳ የተሻለ ቅንጅት እንደነበረው የቢቢሲ ዘገባ የሚያሳይ ሲሆን 43 በመቶ የሚሆኑ ድምፅ ሰጪዎችን የዲሞክራቲክ ፓርቲ ደጋፊዎች አነጋግረዋል፡፡ በተቃራኒው የማኬን ደጋፊዎች 33 በመቶ የሚሆኑ ድምፅ ሰጪዎችን ብቻ አግኝተዋል፡፡

ሰኞ እለት በብዙ ስቴቶች በተጠናቀቀው የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ አዲስ አራት ሚሊዮን ድምፅ ሰጪዎች ብዙሀኑ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተመዝጋቢዎች መሆናቸውን፤ በዚህም ፍሎሪዳ በምሳሌነት እንደምትጠቀስ ተገልጿል፡፡

ከኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት ሳራ ፔሊን ድምፅ ሰጪዎች ባራክ ኦባማ ከቀድሞ የቤተክርስቲያን ፓስተር ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

"ስለፓስተሩና (ስለአሜሪካ መጥፎነት የሚሰበኩ ናቸው) ስለ ኦባማ ግንኙነት በሰፊው የማይወራበት ምክንያት አይገባኝም፡፡ ያ ፓስተር ስለታላቋ አገራችን አሜሪካ የተናገራቸው ነገሮች በሙሉ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው" ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ የኦባማ የዘመቻ ቡድን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ከ2ዐ ዓመት በፊት ተፈፅሞ በነበረ የገንዘብ ቅሌት ሚስተር ማኬይን ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የኦባማ የዘመቻ ቡድን በሳምንቱ መጨረሻ ለደጋፊዎች በኢ-ሜይል በላኩት የኢንተርኔት ቪድዮ ሚስተር ማኬይን በገንዘብ ማጭበርበር የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ከአሪዞናው ባለሀብት ቻርልስ ኪቲንግ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት አሳውቋል፡፡
Last Updated ( Thursday, 09 October 2008 )
 
< Prev   Next >