| ማህበሩ ከ417 ሚሊዮን... |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
|
ማህበሩ ከ417 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘ
ማህበሩ በበጀት ዓመቱ አንድ ሚሊዮን 712 ሺ 354 ቶን ዕቃ ለማጓጓዝ ታቅዶ 2 ሚሊዮን 224 ሺ 648 ቶን ዕቃ ማጓጓዙን፣ ይኸም ከዕቅዱ 129 በመቶ መሆኑን፣ የዓመቱ ጠቅላላ ገቢ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ታቅዶ፣ የተጓጓዘው ዕቃ መጠን ጨምሮ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በማስገባት 108 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል፡፡ (አዲስ ዘመን፣ መስከረም 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም". ለ280 አካል ጉዳተኞች ዕርዳታ ተሰጠ በምዕራብ ሐረርጌ ለ280 አካል ጉዳተኞች ተሽከርካሪ ወንበር፣ የከንፈር መሰንጠቅ ጉዳት ለደረሰባቸው የቀዶ ህክምና መደረጉን የዞኑ ሕዝብ አደረጃጀት ሠራተኞና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡ የአካል ጉዳይ ያለባቸው 13ዐ ሰዎች ለመንቀሳቀሻ የሚያገለግላቸው ተሽከርካሪ ወንበር፣ የከንፈርና ድድ መሰንጠቅ ለደረሰባቸው 15ዐ ሰዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) የቱሪዝም መስህቦችን ለማስተዋወቅ ሰነድ ተዘጋጀ የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህቦች መልካም ገፅታ በውጭው ዓለም በማስተዋወቅ ረገድ አቅጣጫ የሚያሳይ የገበያ ስትራቴጂክ ሰነድ ማዘጋጀቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ስትራቴጂክ ሰነዱ መስህቦችን የማስተዋወቁ ሥራ ሊተኮርባቸው የሚገባቸውን ሀገሮች ዝርዝር መለየቱን፣ በስትራቴጂክ ጥናቱ መሠረት በዓለም አቀፍ የጉዞና የቱሪዝም ንግድ ትርኢቶች ላይ በመሳተፍ የሀገሪቱን መስህቦች የማስተዋወቅ ሥራ መካሄዱን አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) የአርሶ አደሮቹ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ10 ብር በላይ ደረሰ በምዕራብ ጐጃም ዞን ጃቢጣህናን ወረዳ በተቀናጀ የግብርና ኤክስቴንሺን ፓኬጅ የታቀፉ አርሶ አደሮች ዕለታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ1ዐ ብር በላይ መድረሱን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ገለፀ፡፡ የአርሶ አደሮቹ ገቢ በአጭር ጊዜ ያደረገው በተሳተፉባቸው በእንስሳት፣ በተፈጥሮ ሀብትና ሰብል ልማት ዘርፎች ከባለሙያ የሚሰጣቸውን ምክር ተቀብለው ሌት ተቀን በመስራት መሆኑን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ " ሜሪጆይ የእግር ጉዞ ኘሮግራም አዘጋጀ "ኃላፊነቴን ለመወጣት እጓዛለሁ" በሚል መርህ ታላቅ የእግር ጉዞ ኘሮግራም ህዳር 7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. እንደሚያካሂድ ሜሪ ጆይ የልማት ተራድኦ ድርጅት አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ባዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ ከ2ዐ ሺ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ፣ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰበት ያለውን "ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን" የሚለውን የልማት መርሃ ግብር ለማስፋፋትና ለማጠናከር ከሚረዱት ዝግጅቶቹ አንዱ መሆኑን ገልፆ፣ በዕለቱ መነሻና መድረሻው መስቀል አደባባይ እንደሚሆንና ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡ (የድርጅቱ መግለጫ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |