Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow በመፈናቀል አደጋ ውስጥ...
በመፈናቀል አደጋ ውስጥ... E-mail
Sunday, 12 October 2008

ImageImageበመፈናቀል አደጋ ውስጥ የወደቁ የኪራይ ቤቶች ተገልጋዮች
በፍሬው አበበ

ሰሞኑን የፌዴራል የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ በ100ዎች በሚቆጠሩ ቅሬታ አቅራቢዎች በተደጋጋሚ ሲንኳኳ ሰንብቷል፡፡ የቅሬታው መነሻም የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ (የቀድሞ ኪራይ ቤቶች አስተዳደር) "ሕገወጥ" ናቸው የሚላቸው ነገር ግን ቤቱን የያዙ ሰዎች ለማስወጣት እንቅስቃሴ የመጀመሩ ጉዳይ ነበር፡፡

 

የችግሩ መነሻ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ታህሳስ 3 ቀን 2000 ዓ.ም ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ወደ መንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ስያሜው እንዲቀየር የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 555/2000 ሲያፀድቅ ከዚሁ ጋር አብሮ በሕገወጥ መንገድ ቤት ይዘዋል ያላቸውን ግለሰቦች በኃይል ጭምር የማስወጣት ሥልጣን ከፍ/ቤት ወደ ኤጀንሲው አዛወረ፡፡ በወቅቱ አንዳንድ የም/ቤቱ አባላት ኤጀንሲው ራሱ አከራይ፣ ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ ውሣኔ ሰጪ የመሆኑ ጉዳይ ሳይዋጥላቸው ቀርቶ ቅሬታ ቢጤ ቢያነሱም የሚሰማቸው አልነበረም፡፡ በዚህ ሁኔታ ኤጀንሲው ፈረንጆች ኢቪክሽን ፓወር የሚሉትን ወይም ኤጀንሲው በራሱ መንገድ የሚፈልገውን ቤት የሚያስለቅቅበት ሥልጣን አስገኝቶለታል፡፡

በወቅቱ ኤጀንሲው ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ውዝፍ የኪራይ ዕዳ አለመሰብሰቡ፣ ከ5 ሺህ በላይ ተከራዮች የመንግሥት ቤቶችን ያለ ውል መያዛቸውን፣ አንዳንዶችም ሕገወጥ ግንባታ ማከናወናቸውን ገል"ል፡፡ ኤጀንሲው እነዚህን ጉዳዮች ፍ/ቤት ሲወስድ መቆየቱ ከጉዳዮቹ መጓተትና ተፈላጊውን ፍርድ ካለማግኘት ጋር በተያያዘ ሕልውናውን ጭምር ሲፈታተን መቆየቱን ይገልፃል፡፡

የኢቪክሽን ሥልጣን ትግበራ

ኤጀንሲው ውል አላደሰም፣ የቁልፍ ሽያጭ አካሂደዋል የመንግሥት ቤት በውርስ ይዘዋል ሕገወጥ ግንባታ አካሂደዋል፣ የተጠራቀመ የኪራይ ዕዳ አለባቸው ያላቸውን እና በመሳሰሉት ምክንያቶች የፈረጃቸውን ተገልጋዮች በ10 ቀናት ቤቱን እንዲያስረክቡት የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ማድረስ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በደብዳቤው ላይ ተገልጋዮች በ10ኛው ቀን በር ከፍተው እንዲጠብቁ፣ ይህ ሳይሆን በር ተሰብሮ ዕቃ ወደ መጋዘን እንደሚጫን በሰላም ተገልጋዮቹ የትራንስፖርትና የመጋዘን ወጪ እንደሚከፍሉ ያስጠነቅቃል፡፡ አንዳንዶች የኤጀንሲውን ይህንን አባባል በደርግ ሰውና ሰው ተጋድሎ የጥይት ክፈሉ ከሚባልበት ዘመን ጋር ያነፃፅሩታል፡፡

የአሠራር መዘበራረቅና አድሎአዊነት

የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ጥቅምት 3 ቀን 1998 ዓ.ም ባደረገው 94ኛ መደበኛ ስብሰባ አምስት አጀንዳዎች መካከል የመጀመሪያው "በድርጅቱ ቤቶች ያለውል ስለሚኖሩ 702 ሰዎች የቀረበውን ጥናታዊ ሪፖርት ተመልክቶ ውሣኔ መስጠት" የሚል ይገኝበታል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ የሚያይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለቦርዱ የውሣኔ ሀሳብ ቀርቦ በዕለቱ በፀደቀው መካከል የግል ቤት በራሱና በባለቤቱ ስም የሌለው ከክ/ከተማና ከቀበሌ ማስረጃ ማቅረብ የሚል፣ የቤቱን የጠቅላላ ውዝፍ ኪራይ ዕዳ በቀድሞ የኪራይ ተመን ሂሳብ ከ10 በመቶ ቅጣት ጋር በአንድ ጊዜ አውሎ ማቅረብ የሚችል ከሆነ፣ ድርጅቱ ቀደም ሲል የተከራይ አከራይ ጉዳዮችን ለማስተናገድ ባወጣው የተለያዩ ደረጃዎች ያሉት የኪራይ ተመን መሠረት ውል ለመሙላት ፈቃደኛ የሆነ፣ የሦስት ወራት የቤትን ኪራይ በመቀጫነት ለድርጅቱ ገቢ የሚያደርጉ ከሆነ እና ተጨማሪ ግንባታ በተካሄደባቸው ቤቶች ላይ በሚወስደው ልኬት መነሻነት ተጨማሪ የሚሆነውን የኪራይ ተመን ለመክፈል ፈቃደኛ ከሆነ በፍ/ቤቱ የተያዘው ክስ ቆሞ የኪራይ ውል በመሙላት ሕጋዊ እንዲሆን ወስኗል፡፡

ሆኖም ጉዳያቸው ከመጋቢት 4 ቀን 1997 ዓ.ም በፊት የፍ/ቤት ውሳኔ ያገኘ ከሆነ፣ ከመጋቢት 4 ቀን 1997 በኋላ በቁልፍ ሽያጭ የተካሄደ ዝውውር ወይም በሕገወጥ አሠራር የተላለፉ ከሆነ ቤቶቹን በሕግ አግባብ ብቻ አስለቅቆ ድርጅቱ እንዲረከብ ወስኗል፡፡

ውሣኔው በተጨማሪም ቀርበው ያልተመዘገቡና በዚህ ጥናትና ውሣኔ የሚካተቱ ሊስተናገዱ እንደሚገባ ጠቅሷል፡፡

ሆኖም ኤጀንሲው የ702 ግለሰቦችን ጉዳይ ከተመለከተና "ሕገወጥ ናቸው" የሚሏቸውን ሕጋዊ ካደረገ በኋላ ለተመሳሳይ ባለጉዳዮች በሩን መዝጋቱን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይገልፃሉ፡፡

29 ያህል ተገልጋዮች በጋራ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት የኢፌዲሪ የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ጉዳዩን አጣርቶ ለ702 ባለጉዳዮች ቦርድ በሰጠው ውሣኔ መሠረት የእነዚህም ጉዳይ ሊታይ ይገባል የሚል አቋም መያዙንና ይህንንም በደብዳቤ ለኤጀንሲው ቦርድ የካቲት 6 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ሆኖም ቦርዱም ሆነ ኤጀንሲው ተጨማሪ አቤቱታዎችን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ተገልጋዮቹ ይገልፃሉ፡፡ በዚህም በአንድ አገር፣ በአንድ ዓይነት ጉዳይ የተለያየ ውሣኔ በመስጠት አድልኦ እንደተፈፀመባቸው ያስረዳሉ፡፡

የተገልጋዮቹ ቅሬታ

አብዛኛዎቹ ቅሬታ አቅራቢዎች ቀደም ሲል የኤጀንሲው ቦርድ ለ702 ባለጉዳዮች የሰጠውን ዕድል የሚያሟሉ መሆኑን በመግለፅ ተመሳሳይ ዕድል እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ጉዳያቸውን ለሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አቅርበው ይሁንታን ቢያገኙም ኤጀንሲው አሻፈረኝ በማለቱ እምባቸውን የሚያብስ አጥተው ከቤታቸው በጠራራ ፀሐይ እየተባረሩ ያሉ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡

በቀድሞ ወረዳ 6 ቀበሌ 11 በአሁኑ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ 10/11/12 ቤት ቁጥር 354 ነዋሪ የሆኑና የአባታቸውን የአቶ አርአያ ኪዳኔ በውርስ ያገኙትን ቤት ተከራክረው ካስመለሱ ከ21 ዓመት በኋላ "ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተቋቁሟል ተብሎ በጋራ ቅሬታችንን አቅርበን፡፡ ቅሬታችሁን በጋራ ማቅረብ አትችሉም፣ በተናጠል አቅርቡ ተባልን፡፡ በተናጠል አቀረብን፡፡ የሰጠነውን ገልብጠው ተቀባይነት አለማግኘቱን ለጠፉልን፡፡" ሲሉ አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ ቅሬታ ይናገራሉ፡፡

ከ200 በላይ ተገልጋዮች የአቤቱታ ደብዳቤ ለጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ አቅርበው እስከ ዓርብ ዕለት ከሰዓት በኋላ ድረስ ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑን የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ኤጀንሲውም የኃይል እርምጃ መውሰዱን አለማቆሙ እንዳሳዘናቸው ይናገራሉ፡፡

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ካሣሁን ወ/ጊዮርጊስ ስለጉዳዩ ተጠይቀው አቤቱታ አቅራቢዎቹ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታቸውን ማቅረብ ይችላሉ የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ሚኒስቴሩ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን ተገልጋዮች አቤቱታ ለማየት እንዲቻል ከመስከረም 13 ቀን 2001 ጀምሮ መመሪያ ወጥቷል፡፡ በመመሪያው መሠረት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር፣ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የተውጣጣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተመስርቷል፡፡ ይህው ኮሚቴ ገለልተኛ በሆነ መልኩ የቅሬታ አቅራቢዎችን አቤቱታ እየተመለከተ ነው ብለዋል፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ግን ኮሚቴው ቅሬታቸውን በቅንነት ለማየት አቅሙም ፍላጎቱም የለውም ይላሉ፡፡   
Last Updated ( Monday, 13 October 2008 )
 
< Prev   Next >