Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ኃይል ቆጣቢ ፍሎረሰንት...
ኃይል ቆጣቢ ፍሎረሰንት... E-mail
Sunday, 12 October 2008

ኃይል ቆጣቢ ፍሎረሰንት አምፖሎች ሊሰራጩ ነው
በብርሃኑ ፈቃደ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከዓለም ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ኃይል ቆጣቢ ፍሎረሰንት አምፖል በቀጣይ ሦስት ወራት ጊዜ ለማሰራጨት ማቀዱን አስታወቁ፡፡

 

አቶ አለማየሁ ተገኑ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር የነፋስ ኃይል ፕሮጀክት ስምምነት ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር፣ በየመኖሪያ ቤቱ የሚገኝ አምፖሎችን፣ የፍሎረሰንት ሥሪት በሆኑና ብቁ የኃይል ጠቀሜታ ባላቸው አምፖሎች ለመተካት ታስቧል፡፡

በአቶ አለማየሁ ገለፃ መሠረት በቀጣይ ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማሰራጨት የታቀደው አምፖሎች ብዛት አራት ሚሊዮን ሲሆን፣ የአምፖሉ ሥርጭት በምን መልኩ ለማድረግ እንደታሰበ የገለፁት ነገር የለም፡፡

በኢትዮጵያ በአብዛኛው ዝቅተኛና መካከለኛ ዜጎች የሚጠቀሙበት አምፖል ከ100 ዓመት የነበረ ቴክኖሎጂ ከመሆኑም ባሻገር ኃይል ቆጣቢ ባለመሆኑ በተጠቃሚው ላይ ተጨማሪ ክፍያ እንደሚያስከትል፣ ኮርፖሬሽኑንም ተጨማሪ ኃይል የሚጠይቀው በመሆኑ፣ በኃይል ቆጣቢ አምፖሎች ለመቀየር መታሰቡ ታውቋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በተመሳሳይ መንገድ ኃይል ቆጣቢ የሆኑ የእንጀራ ምጣዶችንና የማብሰያ ምድጃዎችን በማስተዋወቅ የማይቆጥቡትን ለመተካት ዕቅድ እንዳለውም አቶ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በተለይ በ2000 ዓ.ም የገጠመውን የኃይል እጥረት ለመፍታት ግድቦችን ከመገንባትና ሌሎች የኃይል አማራጮችን ከማፈላለግ ጎን ለጎን የኃይል አጠቃቀምን በቁጠባና በሥርዓት እንዲመራ ጥረት እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ ተገዝተው ስለሚሰራጩት የፍሎረሰንት አምፖሎች ጉዳይ የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ ተጨማሪ ማብራሪያ ተጠይቀው በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት በመግለጽ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡
 
< Prev   Next >