| የደቡብ አፍሪካው ኤ.ኤን.ሲ... |
|
| Sunday, 12 October 2008 | |
|
በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከኤ.ኤን.ሲ መገንጠል የሚያስችል ውሳኔ ለማስተላለፍ ኮንፈረንስ እንደሚካሄድ ባስታወቁበት ጊዜ ሚስተር ሌኮታ በአሁኑ ሰዓት በኤ.ኤን.ሲ ውስጥ የሚገኙት ሁለቱ የተለያዩ ወገኖች (የዙማ እና የሞቤከ ደጋፊዎች) መረቻቸው መቃረቡን ተናግረዋል፡፡ በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ በደቡብ አፍሪካ ጠቅላይ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ገዥው ፓርቲ በዙማ ደጋፊዎችና በምቤኪ ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ተከፋፍሏል፡፡ ሚስተር ሌሊታ የኤ.ኤን.ሲ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡ "በአጭር ጊዜ ውስጥ የዚችን አገር ዴሞክራሲ ለመከላከል የሚያስችለንን ውሳኔ ለማስተላለፍ ስንል ጓደኞቻችንና ሌሎች አጋሮቻችንን ብሄራዊ ስብሰባ ለመጥራት አስበናል" ሲሉ ሌኮታ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ "የኤ.ኤን.ሲ አመራር በዚህ እብሪተኛነቱ ከቀጠለ ቀጣዩን እርምጃ እንወስዳለን" ያሉት ሚስተር ሌኮታ ሚስተር ዙማን በስም ገልጸው ባይናገሩም ጎሰኛነትንና በሕዝብ መድረክ ቆመው ግጭት የሚቀሰቀስ ዘፈን የሚዘፍኑትን የኤ.ኤን.ሲ መሪዎችን አውግዘዋል፡፡ ሌኮታ በተዘዋሪ "ብሪንግ ማይ ማሽን ጎን (ጠበንጃዬን አምጡ"" እያሉ የሚዘፍኑትን ሚስተር ዙማን እየተቹ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የተወሰኑ የዙማ ደጋፊዎች ዙማ የዙሉ ተወላጅ በመሆናቸው ይደሰታሉ፡፡ ሚስተር ሌኮታ ባለፈው ሳምንት በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ አዲስ የኤ.ኤን.ሲ አመራር ዴሞክራሲን እየደፈጠጠ ነው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡ የዙማ ደጋፊዎች የዙማን ጉዳይ ሲመለከት በነበረው የፍትህ አካል ዛቻ ሲሰነዝሩ ነበር ተብለው መወንጀላቸው ይታወሳል፡፡ የኤ.ኤን.ሲ የወጣት ሊግ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ለዙማ ሲል ሰዎችን ለመግደል ተዘጋጅቶ እንደነበር ተናግሯል፡፡ የሚስተር ዙማ ደጋፊ የሆኑት የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጆፍ ራዴሌ በበኩላቸው ሚስተር ሌኮታና እርሳቸውን የሚደግፉ ሰዎች ፓርቲውን ለቀው መሄድ ይችላሉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ሞቤኪ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ የተደረጉት በሚስተር ዙማ የሙስና ውንጀላ ጣልቃ ገብተዋል በማለት ኤ.ኤን.ሲ ስልጣን እንዲለቁ ከጠየቃቸው በኋላ ነው፡፡ የምቤኪን ከስልጣን መውረድ ተከትሎ ራሳቸውን ከስልጣን ካገለሉት በርካታ ሚኒስትሮች መካከል አንዱ ሚስተር ሌኮታ ናቸው፡፡ ሚስተር ምቤኪ ግን የቀረበላቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል፡፡ ኤ.ኤን.ሲ የመገንጠል አደጋ ላይ ወድቋል ለሚለው ሹክሹክታ ምላሽ የሰጡት ታቦ ምቤኪ ወሬና ለትንሽ ቀን ብቻ የሚቆይ ነው ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል፡፡ "ይህ ወሬ ረጅም ዕድሜ ይኖረዋል ብዬ አላስብም በኤ.ኤን.ሲ እና በኤ.ኤን.ሲ ፖሊሲ የማያምን አካል ከኤ.ኤን.ሲ ጋር ተመሳሳይ ፖሊሲ ያለው ድርጅት ሲፈጥር መመልከት አስቂኝ ነው፡፡" የቢቢሲው ጆናህ ሊሸር ከጆሀንኪበርግ እንደዘገበው አዲስ የሚመሰረተው ፓርቲ በሚቀጥለው አመት በሚካሄደው ምርጫ የፖለቲካ ተፎካካሪ ለመሆን ይቸገራል፡፡ ጋዜጠኛም እንደሚለው ሚስተር ምቤኪና የኤ.ኤን.ሲ የረጅም ጊዜ አባል የነበሩ ሰዎች የሚገነጠለው ፓርቲ የመቀላቀላቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት እሁድ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የኖቤል ሽልማት አሸናፊው ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ደቡብ አፍሪካ ከኤ.ኤ.ን.ሲ ሌላ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ ቢኖራት እንደሚመርጡ ገልጸዋል፡፡ ዴዚሞንድ ቱቱ እንደሚሉት ከሆነ የሚስተር ምቤኪ ከስልጣን መወገድ አሁን የተፈጠረውን አመጽ ለመቀስቀስ ምክንያት ቢሆንም በፓርቲው ውስጥ ያለው ችግር ቆየት ያለእና ስር የሰደደ ነው፡፡ ሚስተር ሌኮታ ለኤ.ኤን.ሲ በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ ኤ.ኤን.ሲ ለደቡብ አፍሪካ ኮሚዩኒስት ፓርቲ (SALP) የአመራር ቦታ መስጠቱን ተችተዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ኮሚዩኒስት ፓርቲ (SALC) በአፓርታይድ ጊዜ ከነበረው ትግል ከሶቪየት ሕብረት መሳሪያ እና ገንዘብ እያመጣ ለኤ.ኤን.ሲ ያቀብል ነበር፡፡ ሚስተር ሌኮታ እንደሚሉት የኤ.ኤን.ሲ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ማዋዴ ማንታሽ የደቡብ አፍሪካ ኮሚዩኒስት ፓርቲ ሊቀመንበር በመሆናቸው በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ያለው ልዩነት እየደበዘዘ መጥቷል፡፡ በሚቀጥለው አመት ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሚስተር ዙማ ፕሬዚዳንት ከሆኑ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደማይቀይሩ አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ሚስ ሄለን ዙሌ ከኤ.ኤን.ሲ የሚገነጠል ወገን በፓርቲያቸው እንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ እንደማይፈጥርባቸው ገልጸዋል፡፡ "እኛ የመሰረትነው ፓርቲ ዘርን ሳይሆን መርህን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ከኤ.ኤን.ሲ የሚገነጠለው ፓርቲ ምንም ስጋት አይሆንብንም፡፡ አሁን እያወራን ያለነው ገና ስላልተፈጠረ ፓርቲ ነው፡፡ ፓርቲው ቢመሰረት እንኳን አባላትን ለመሰበሰብ ብዙ ጊዜ ስለሚወስድበት የእኛ ተፎካካሪ አይሆንም" ብለዋል፡፡ የዴሞክራቲክ አሊያንስ ፓርቲ መሪዋ እንደሚሉት የእርሳቸው ፓርቲ በሕገ መንግሥት የበላይነት የሚያምን በመሆኑ ማንንም ፓርቲ አይፈራም፡፡ |
|
| Last Updated ( Monday, 13 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |