| የአለም የገንዘብ ቀውስ በልማትና... |
|
| Sunday, 12 October 2008 | |
|
የአለም የገንዘብ ቀውስ በልማትና ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል
በአለም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በመፍጠር የብዙዎችን ሕይወት እየተፈታተኑ ከሚገኙ ችግሮች መካከል በግንባር ቀደምነት የሚዘረዘሩት እያደጉ የመጡት የገቢና የሃብት አለመመጣጠን ችግሮች፣ የአየር ሚዛን ለውጥ፣ የምግብና የሃይል አቅርቦቶች ዋጋ መጨመር ጥቂቶቹ ሲሆኑ በቅርቡም ከቁጥጥር ወጭ እየሆነ የመጣው የገንዘብ ቀውስ በአፍሪካ የሚካሄዱ የኢኮኖሚ ልማትና የእድገት ሂደቶችን ሊያስተጓጉሉ እንደሚችሉ ያላቸውን ሥጋት አስቀምጠዋል፡፡ ሐሙስና አርብ አዲስ አበባ በአፍሪካ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የአለም የሥራ ድርጅት በቅርቡ "ማህበራዊ ፍትህ ለሚዛናዊ ሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን"" አዋጅን ከአፍሪካ እይታ አንፃር በማስመልከት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ የወጣው አዋጅ ለአፍሪካ አገሮች የተሻለ የሥራ ዕድል፣ የማኅበራዊ ዋስትና፣ ማኅበራዊ ውይይትና ተሳትፎ እንዲሁም በርካታ ጥቅሞችን የሚያስገኝ እንደሆነ በልዩ ስብሰባው ላይ የተመለከተ ሲሆን ከየአገሮቹ የተውጣጡ ሚኒስትሮች፣ አሰሪዎችና ሠራተኞች፣ በአፍሪካ የአለም ሥራ ድርጅት ዳይሬክተሮች እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በስብሰባው ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በላኩት መግለጫ በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ የሚገኘው የምግብ ዋጋ ብዙ ድሆችን ክፉኛ የመታ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የአለም የሥራ ድርጅት ይፋ ያደረገው መረጃ እንዳመለከተው ከመጋቢት 1999 እስከ መጋቢት 2000 ዓ.ም በነበረው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከምግብ እህሎች ውስጥ የስንዴ ዋጋ 130 በመቶ እንዲሁም የሩዝ ዋጋ 74 በመቶ የሆነ ጭማሪ ታይቶባቸዋል፡፡ በሚያዚያ ወር 2000 ዓ.ም የሩዝ ዋጋ በኪሎ ከዘጠኝ ብር በላይ ሆኗል፡፡ ይህም አምና በጥር ወር ለአንድ ኪሎ ይወጣ የነበረው አማካይ ገንዘብ ሦስት ብር በመሆኑ ከሦስት እጥፍ በላይ መጨመሩንና የምግብ ዋጋዎች መናር በመልካም ሥራ፣ በድህነት ቅነሳና በቅጥር ሁኔታዎች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ አመላካች እንደሆነ የሚጠቁመው የአለም የሥራ ድርጅት መረጃ በአገሮች የማክሮ ኢኮኖሚ ላይም የራሳቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ያስታውሳል፡፡ በተለይ በበጀት እጥረት፣ በንግድ ሚዛን መዛባትና በዋጋ ንረት በኩል ቀላል የማይባል ቀውስ እየፈጠሩ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ያገኛሉ ተብሎ እንደማይታሰብም ይጠቁማል፡፡ ለዚህ አብነት ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ በኢኮኖሚ እያደጉ ያሉ አገሮች የገቢ መጠን መጨመር እና የባዮ ፊውል ምርት መንሰራፋት ይጠቀሳሉ፡፡ በባዮ ፊውል በኩል በተለይ አሜሪካ በአመት ለኢታኖል ምርት ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ የኃይል አቅርቦቷን እንደምታሟላና ለዚህም ተግባር የበቆሎ ምርትን እንደ ዋና ግብዓት የምትጠቀም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል በግብርና ላይ የሚካሄደው ኢንቨስትመንት መቀነስ፣ የእህል ክምችት መዳከም፣ የመሬትና የውሃ አቅርቦት እጥረት በዋና ምክንያትነት ከሚጠቀሱና ለምግብ መናር አስተዋጽኦ ካደረጉ ምክንያቶች ተርታ የሚመደቡ ሆነዋል፡፡ |
|
| Last Updated ( Sunday, 12 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |