Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ለአዲስ አበባ መንገድ ግንባታ ከ22 ...
ለአዲስ አበባ መንገድ ግንባታ ከ22 ... E-mail
Sunday, 12 October 2008

ለአዲስ አበባ መንገድ ግንባታ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል
በዳዊት ታዬ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ለመንገድ ልማት ያስፈልጋል ብሎ በእቅድ የያዘው ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ቢሆንም አሁን ያለው የኮንስትራክሽን እቃዎች ዋጋ መወደድ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ሊያደርሰው እንደሚችል ተገለፀ፡፡

 

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ሀይሌ ለሪፖርተር እንደገለጹት የአዲስ አበባን የመንገድ ልማት ለማከናወን በተያዘው መሪ እቅድ መሠረት እስከ 2007 ድረስ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ቢሆንም አሁን ያለው የኮንስትራክሽን እቃዎች ዋጋ ከተገመተው በላይ ሃያ እና ሰላሳ በመቶ ሊጨምር የሚችል በመሆኑ ለመንገድ ግንባታ ያስፈልጋል ተብሎ በእቅድ ተይዞ የነበረው ወጪ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

በእቅዱ መሰረት በየአመቱ እስከ መቶ ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው መንገድ ይሰራል ተብሎ የታቀደ ሲሆን በአምስት አመታት ውስጥ 500 አዳዲስ ኪሎ ሜትር የሚደርስ የመንገድ ግንባታ ለማካሄድ ያስችላል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለአዲስ አበባ የመንገድ ልማት የሚውለውን ገንዘብ የሚሸፍነው የከተማው አስተዳደር ሲሆን ይህ ለመንገድ ልማት የሚወጣው ወጪ በአዲስ አበባ አስተዳደር ብቻ መሸፈን የሌለበትና ሌሎች አማራጮች መፈለግ እንደሚኖርበትም ገልጸዋል፡፡ እንዲህ ያለ ትላልቅ የመንገድ ልማት የሚከናወኑ አገሮች የፋይናንስ ምንጫቸውን ያሰፋሉ፡፡ በዚህ ረገድ አዲስ አበባ ለየት የምትል መሆንዋንም ይጠቅሳሉ፡፡

እንደ አቶ ፍቃዱ ገለጻ ለከተማዋ የመንገድ ልማት የሚውለውን ገንዘብ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት እንዲያገኙ ማድረግ ካልተቻለ በአስተዳደሩ በሚመደበው በጀት ብቻ እቅዱን ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል፤ በዚህ የመንገድ ልማት የፌዴራል መንግሥትም እገዛ ሊኖር እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ ያለው የመንገድ 2500 ኪ.ሜ ገደማ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ፍቃዱ ከዚህ ውስጥ በአስፓልት የተሸፈነው 1100 ኪ.ሜትሩ ብቻ ነው፡፡ ቀሪው ደግሞ የጠጠር መንገድ በመሆኑና ከተማዋ ሊኖራት ከሚገባው የ3000 ኪ.ሜትር የአስፓልት መንገድ ጋር ሲነፃፀር አሁን ያለው የመንገድ ርዝማኔ ዝቀተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡  
 
< Prev   Next >