| የመጀመሪያው የንፋስ ኃይል... |
|
| Sunday, 12 October 2008 | |
|
ባለፈው ሐሙስ በሒልተን ሆቴል በኮርፖሬሽኑና በፕሮጀክቱ ባለቤት ቨርኔት ግሩፕ መካከል በተካሄደ የስምምነት ፊርማ ስነሥርዓት ወቅት እንደተገለፀው የንፋስ ኃይል ማመንጫው በአውሮፓ በተለይም በፈረንሳይ ከሚገኘው የበለጠ የሃይል አቅርቦት በኢትዮጵያ ማመንጨት ይችላል፡፡ የቨርኔት ግሩፕ ኩባንያ ባለቤትና ዳይሬክተር የሆኑት ሚ/ር ቨርኔት በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት በፈረንሳይ ትልቁ የነፋስ ኃይል ማመንጫ 2ሺህ 500 ኪሎ ዋት በሰዓት የሚያመነጭ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ 3ሺህ 500 ኪሎ ዋት በሰዓት ለማመንጨት ጥናት የተደረገ በመሆኑ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ከነፋስ ማግኘት እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡ "ይህ ፕሮጀክት በዓለም ደረጃ ሲታይ በመጠኑ ትልቅ ነው" ያሉት አቶ ምህረት በዓመት 120 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ማመንጨት ከመቻሉም በላይ በውሃና በሌሎች የኃይል አቅርቦቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ተስፋ የተጣለበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ኢኮኖሚያዊ አዋጭነቱን በሚመለከት ከሪፖርተር ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ከንፋስ ለሚመነጨው ኃይል በሰዓት እስከ ስድሳ ሳንቲም ገደማ የሚወጣ ሲሆን፣ አሁን ባለው ገበያ እየወጣ ያለው ወጪ በሰዓት ከሦስት ብር በላይ በመሆኑ አዋጪነቱ ጥያቄ የለውም ብለዋል፡፡ የፈረንሳይ የልማት ድርጅት በሚሰጠው የዝቅተኛ ወለድ ብድርና የፈረንሳዩ ቢ ኤን ፒ ፓሪ ባስ የሚባለው ባንክ ባመቻቹት ብድር የሚጀመረው የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት በፈረንሳይ መንግሥት በኩል የመድን ሽፋን ዋስትና እንደተገባለትም ታውቋል፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ የምህንድስና አማካሪና የምህንድስና ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በኮንትራክተርነት የሚሳተፉ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የአማካሪነት ድርሻ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የንፋስ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ የተለያዩ መሳሪያዎችን አገር ውስጥ ለመፈብረክ የሚያስችል ኩባንያ ለማቋቋም ማቀዳቸውን የገለፁት ሚ/ር ቬርኔት ናቸው፡፡ የንፋስ ኃይል ማመንጨት የሚያስችሉ መሳሪያዎችንና ቁሳቁሶችን ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ለማቋቋም እስከ 500 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ያስፈልጋል የሚሉት ሚ/ር ቬርኔት ከ30 እስከ 60 ሚለዮን ብር የሚገመት ካፒታል እንደሚጠይቅም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ ለፕሮጀክቶቹ የሚፈለገው የሰው ኃይል አብዛኛው ከኢትዮጵያ እንደሚሆን የተናገሩት ሚ/ር ቬርኔት በተለይ የምህንድስና ባለሙያዎችና አርክቴክቶች እንደሚያስፈልጉ ታውቋል፡፡ ከአሼጎዳ በተጨማሪ በአዳማና አዘዞ ቦታዎች ላይ ሌላ የነፋስ ኃይል ማመንጨት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ለመትከል መታቀዱንና ከ100 ሜጋ ዋት በላይ የኃይል አቅርቦት ያስገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል፡፡ በቬርኔት ግሩፕ አማካይነት የሚተከሉት የነፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 120 ሲሆኑ፣ እያንዳንዳቸው አንድ ሜጋ ዋት ያስገኛሉ፡፡ ኩባንያው በሌሎችም የአፍሪካ አገሮች የነፋስ ኃይል አቅርቦትን በሚመለከት የሚሰራ ሲሆን፣ በኬፕ ቨርዴ፣ በኬንያ እና በጂቡቲ የሚያካሂዳቸውን ፕሮጀክቶች በዋናነት ጠቅሰዋል፡፡ |
|
| Last Updated ( Monday, 13 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |