Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የአንድ ሰው ዓመታዊ የስጋና...
የአንድ ሰው ዓመታዊ የስጋና... E-mail
Sunday, 12 October 2008

የአንድ ሰው ዓመታዊ የስጋና የወተት ፍጆታ ዝቅተኛ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ሰፊ የከብት ሀብት ቢኖራትም የአንድ ሰው ዓመታዊ የስጋና የወተት ፍጆታ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሲነፃጸር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት የከብት ሀብት ምርምር ሂደት ዳይሬክተር ገለጹ፡፡

 

ለሦስት ቀናት የተካሄደውን የኢትዮጵያ እንስሳት እርባታ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ኮንፈረንስን ዳይሬክተሩ አቶ ስዩም ቢዲዬ መስከረም 28 ቀን 2001 ሲከፍቱ እንዳመለከቱት ሀገሪቱ ከአንድ ከብት የምታገኘውም የምርት ውጤት በአህጉሩ ካሉት አገሮች አኳያ ሲታይ በእጅጉ ዝቅተኛ ነው፡፡

መንግሥትም ይህንኑ በመገንዘብ ድህነትን ለመቀነስ እንዲቻል ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት ባወጣው ፕላን ውስጥ ለከብት ሀብት ልማት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን፣ በዚህም የተነሳ እስከ 2010 በሚቆየው በዚሁ ፕላን ውስጥ አሁን ያለውን የሥጋ ምርት በ48 በመቶ፣ የወተት ምርትን በ55 በመቶ፣ እንዲሁም አሳና የማር ምርትን በ170 እና በ159 በመቶ የማር ውጤት የሆነውን ስም 94 በመቶ፣ እንቁላልን 25 በመቶ ከፍ ለማድረግ ማቀዱን አስረድቷል፡፡

ዶክተር ተድላ ደሴ የማህበሩ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው በእንስሳት እርባታ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው ግለሰቦች ምን አይነት ፖሊሲና ተቋማዊ ድጋፍ ነው የሚደረግላቸው የሚለው ጥያቄ ተገቢ መልስ ማግኘት እንደሚኖርባት አሳስበዋል፡፡

የእንስሳት እርባታና የእርሻ ሥራ ከሌሎች ልማታዊ ዘርፎች በእኩል ደረጃ መታየትና አስፈላጊውም ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባ እንዲሁም የከብት ሀብት ልማትን ለማሳደግ አዲስ ፖሊሲና አደረጃጀት እንደሚስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በዓለም ላይ የተከሰተው የምግብ ቀውስ ወይም ውድነት በእንስሳት እርባታ ላይ በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የሚያስከትለው ተፅእኖ መታየት እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡   

የማህበሩ ዜና መጽሄት በመስከረም እስከ ጥቅምት ልዩ እትም ላይ ካወጣው ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለው የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት የጋማ ከብት፣ በግና ፍየልን የሚያጠቁ በሚል የመዘገባቸው የእንስሳት በሽታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መኖራቸውን አመልክቷል፡፡ ይህም በውጭ ገበያ በሚቀርበው የከብት ሀበት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ጠቁሟል፡፡

በርካታ ሳይንቲስቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የግብርና ልማት ባለሙያዎች፣ የግል ዘርፍና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ በሆኑበትና በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ ኮንፈረንስ ላይ የእንስሳት እርባታን የተመለከቱ 30 ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
 
< Prev   Next >