Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን 50...
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን 50... E-mail
Sunday, 12 October 2008

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን 50 ከመቶ ከፍ ለማድረግ ታቅዷል

መንግሥት የዘመናዊ ኢነርጂ ልማት ጠቀሜታን ከግምት ውስጥ በማስገባት እ.ኤአ እስከ 2010 ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን 50 ከመቶ ለማሳደግ ማቀዱንና ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በማከናወን ላይ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

 

የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ ታዳሽ ኃይሎችን አስመልክቶ መስከረም 30 ቀን 2001 ባካሄደው የግማሽ ቀን አውደ ጥናት ላይ የቀረበው ይኸው ጥናት እንዳመለከተው የትራንስፖርት መሰረተ ልማት መስፋፋት እያደገ መምጣቱ የሚያበረታታ ቢሆንም ከነዳጅ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡

ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እውን መሆን ኢነርጂን በብዛትና በጥራት የማቅረቡ ጉዳይ በእጅጉ ወሳኝ መሆኑን ጥናቱ አመልክቶ ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ሲታይ ግን አብዛኛው ሕዝብ ባለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ሳቢያ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን በጥራትና በብዛት እንደማያገኝ አስረድቷል፡፡

ኢትዮጵያ ኃይድሮ፣ ባዮማስ ወይም ባዮፊዩል፣ ሶላር፣ ነፋስና ጂኦተርማል የመሳሰሉ ታዳሽ ኃይሎች በብዛት እንዳሏት፣ ነገር ግን በፋይናንስ እና በተቋም ውስንነት የተነሳ በሚገባ እንዳልተጠቀመችባቸው አመልክቷል፡፡

በአክሱም ሆቴል አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ አውደ ጥናት ላይ በሀገሪቱ የሚገኙትን ታዳሽ ኃይሎች ጥቅም ላይ ለማዋልና በሕብረተሰቡም ዘንድ በብዛት እንዲታወቁ ለማድረግ የሚያስችሉ ጠቃሚ ሀሳቦች የተሰነዘሩ ሲሆን ውይይትም ተካሄዷል፡፡
 
< Prev   Next >