| የባህላዊ አንትሮፖሎጂ ጥናቶች... |
|
| Sunday, 12 October 2008 | |
|
ባለሥልጣኑ አዘጋጅቶ ያሳተማቸው የተለያዩ ብሔረሰቦችን ባህላዊ ገጽታዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት የክርስትና ትውፊታዊ የትምህርት ሥርዓት ቅኝታዊ ጥናት ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኔስኮ ጽ/ቤት ድጋፍ የታተሙት በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጁት ደግሞ በደቡብ ኦሞ ዞን በሚገኙ 16 ብሔር ብሔረሰቦች ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ላይ የተደረገ ኢንቬንቶሪ ነው፡፡ በደቡብ ኦሞ ዞን በሚገኙት 16 ብሔረሰቦች በኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ላይ ለ6 ሳምንታት ኢንቬንቶሪ የተደረገበት ዓላማው የብሔረሰቦቹን የማንነት መገለጫዎች የሆኑ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶችን መለየት፣ ማጥናትና ዶክመንት ማድረግ፣ አስፈላጊነትና ጠቃሚነታቸውን በመረዳት ለእይታ እንዲበቁ ማድረግና ያሉበትን ሁኔታና የደረሰባቸውን ጉዳት ተገንዝባ ቀጣይነት እንዲኖራቸው ተገቢውን ጥረት ማድረግ ነው፡፡ በኢንቬንቶሪው የ16ቱ ብሔረሰቦች አፋዊ ትውፊቶች፣ ትውን ጥበባት፣ ማኅበራዊ ክንዋኔዎች፣ ሥነ ሥርዓቶችና ፌስቲቫሎች፣ የተፈጥሮ ዕውቀትና ትግበራዎች የእደ ጥበባት ክህሎት ምድቦች ሥር የሚገኙ 320 አላባውያን (elements) ተገቢውን የባህላዊ አንትሮፖሎጂ የጥናት ስልት በመጠቀም መመዝገባቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የብራይሌና ኦንጎታ ማኅበረሰብን አኗኗርና ባህላዊ እሴት የሚያስቀኝ ጥናታዊ ፊልምም በዲቪዲ መታተሙ ታውቋል፡፡ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ጃራ ኃይለ ማርያም በመልእክታቸው እንደገለጹት፣ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ለአካላዊ፣ ለማኅበራዊና ለኢኮኖሚያዊ (ግሎባላይዜሽንን ጨምሮ) ሥጋቶች የተጋለጡ በመሆናቸው፣ የጥናት ውጤቶች ለኅትመት እንዲበቁ ማድረግ ቅርሶችን ለትውልድ ለማስተላለፍና በኅብረተሰቡ እንዲታወቁ በማድረግ ረገድ ያለው ፋይዳ የላቀ ነው፡፡ |
|
| Last Updated ( Monday, 13 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |