Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow አዲሱ የግብር ጭማሪ የኬንያ...
አዲሱ የግብር ጭማሪ የኬንያ... E-mail
Sunday, 12 October 2008

አዲሱ የግብር ጭማሪ የኬንያ ዳኞችን አስቆጥቷል

በኬንያ የፓርላማ አባላትና ህገ መንግሥታዊ ጽ/ቤት ውስጥ ሠራተኞች ላይ የተጣለው ግብር በመስከረም ወር ደመወዛቸው ላይ ቅናሽ በማሳየት ዳኞችን ተጎጂ ማድረጉን ዘስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

 

ጉዳዩ 50 የከፍተኛ ፍርድ ቤትንና 10 የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱን ዳኞች የበጠበጠ ሲሆን ዳኞቹ ከሲቪል ሰርቪስ ዋና ተጠሪ ፍራንሲስ ሙታውራ ጋር ለመነጋገረ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ከዳኞቹ አንዱ ብቻውን ከወር ደመወዙ ላይ ከ10"000 ብር በላይ ተቆርጦበታል፡፡

የግብር ጭማሪው የተወሰነው የቀድሞው የአገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር አሞስ ኩሙንያ በህገ መንግሥታዊ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች ዳኞችን፣ አቃቤ ሕግን፣ የህዝባዊ አገልግሎት ኮሚሽነርን፣ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነርንና ተቆጣጣሪን፣ ዋናው ኦዲተርንና የፓርላማ አባላትን ጨምሮ በሚያገኙት ደመወዝና የተለያዩ አበሎች ላይ ግብር እንዲጣል ባቀረቡት የውሳኔ ሃሳበ መሰረት ነው፡፡
 
< Prev   Next >