| የግብጽ ፕሬዚዳንት ዋና አዘጋጁን... |
|
| Sunday, 12 October 2008 | |
|
የአል-ዱከቱር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የፕሬዚዳንቱ ዋነኛ ተች የሆነው ዋና አዘጋጁ ኢብራሒም ኢሳ ባለፈው ወር የሁለት ወራት እስራት የተፈረደበት በጋዜጣው ላይ የወጣው ጽሁፍ በፍርድ ቤቱ እይታ የህዝብ ደህንነትን የሚያውክ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ በአገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ፕሬዚዳንቱ በታጠቁ ሃይሎች ቀን ይቅርታ ያደረጉለት ለሃሳብ ነፃነት ትኩረት እንደሚሰጡ ለማረጋገጥ መሆኑን ተገልጿል፡፡ የ80 ዓመቱ ፕሬዚዳንት በእሳቸውና በማንኛውም የግብጽ ዜጋ መካከል ዘላቂ አለመግባባት እንዲፈጠር እንደማይፈልጉም ይፋ አድርገዋል፡፡ የቡሽ አስተዳደር ቃል አቀባይ ባለፈው ዓመት ዋይት ሃውሰ በግብጽ ዋና አዘጋጆች ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና እንግልት እንደሚያሳስባት ገልፀው ነበር፡፡ |
|
| Last Updated ( Monday, 13 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |