Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በቀኝ ሰጥቶ በግራ መቀበል
በቀኝ ሰጥቶ በግራ መቀበል E-mail
Sunday, 12 October 2008

በናታን ዳዊት

ከቅርብ አመታት ወዲህ በተለይም ባሳለፍናቸው ሁለት ዓመታት በአገራችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ሰብሎች ዋጋ ጣራ መንካት፣ በቂ አቅርቦት አለመኖር የዜጎችም የመንግሥትም ራስ ምታት ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ችግር ሥር ነቀል የሆነ ፈውስ አላገኘም፡፡ ይህ የሁሉንም ሸማች የተፈታተነውን የኑሮ ውድነት ቢያንስ ለማረጋጋት የተሞከሩ ሙከራዎችም ጊዜያዊ መፍትሄ ከመሆን ሊዘሉ አልቻሉም፡፡

 

በአገራችን ደረጃ መንግሥት በምግብ ሰብሎች የታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና ቢያንስ ደሃውን ሸማች ለመጥቀም ተብሎ በድጎማ መጣ የተባለውን ስንዴ በየቀዬው የደረሰ ቢሆንም ገበያውን አረጋግቶታል ወይም ዘላቂ መፍትሄ ሰጥቷል ለማለት ባይቻልም መንግሥት ስንዴውን ገበያ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ምንም ለውጥ አላመጣም ወደሚል መደምደሚያ አያደርሰንም፡፡ መንግሥት ላደረገው ለዚህ መልካም ተግባሩ ሸማቹ ምስጋና ማቅረቡ ግን አልቀረም ነበር፡፡

በተለይ የስንዴው ስርጭት ተግባራዊ የተደረገውና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ የተደረገው መንግሥት ድጎማ በማድረጉ ነው መባሉ ይብዛም ይነስም ጊዜያዊ ልንለው የምንችለው እፎይታ ሰጥቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት እንድንሰማ የተደረገው የነዳጅ ጭማሪ ዜና ግን ለወራት በድጎማ ስንዴ መጠነኛ እፎይታ አግኝቶ የነበረው ሸማች ግራ እንዲገባ አድርጎታል፡፡

ይህ ዜና ለሸማቹ ጥሩ ያልሆነበት በርካታ ምክንያቶች ያሉ ቢሆንም በተለይ በእስከ ዛሬው የነዳጅ ጭማሪ ላይ በኬሮሲን (ነጭ ጋዝ) ላይ የተደረገው ጭማሪ ድሃ የምንለውን ሸማች አቅም ያላገናዘበና ጊዜውን ያልጠበቀ፣ ድንገት ደራሽ በመሆኑ ጭምር ነው፡፡ እንደውም ነገሩ ሁሉ በቀኝ ሰጥቶ በግራ መቀበል ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡
 
ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በናፍጣ ላይ የተደረገው ጭማሪ ሲታከልበት ደግሞ ሊፈጥር የሚችለውን የኑሮ ውድነት መገመት ይቻላል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህ ሰበብ የምግብ እህል ዋጋ የባሰ እንዲጨምር ማድረጉ ነው፡፡

የነዳጅ ጭማሪው በተደረገ በቀናት ልዩነት ውስጥ በአንድ ኩንታል የጤፍ ዋጋ ላይ ከ50 እስከ 100 ብር ለውጥ መከሰቱን እንደቀላል ምሳሌ ልንወስድ እንችላለን፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጂ በሌሎች ምርቶች ላይም ጭማሪ እየታየ ነው፡፡

ይህም ጭማሪ ስንዴ በድጎማ ብናስገባና በተመጣጣኝ ዋጋ አከፋፈልን ብንል እንኳ ከሌላ አቅጣጫ በነዳጅ ጭማሪው የሚፈጠሩ የዋጋ ለውጦች ሸማቹን ከሚችለው በላይ እንዲሸከምና እስካሁን የቆየውን የኑሮ ውድነት ይበልጥ እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡

የነዳጅ ጭማሪው መደረጉን ከሚያስታውቀው ዜና ጎን ለጎን ደግሞ ከዚህ በኋላ መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ ማቆሙንም የሚገልጽ በመሆኑ የሰሞኑ የአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ከመምጣቱ ጋር ተዳምሮ የአዲሱ የነዳጅ ጭማሪ፣ በኑሮ ውድነት መላው ጠፍቶት በመቆዘም ላይ ያለውን ሸማች ከግምት በማስገባት ተግባራዊ የሆነ ነው ብሎ ለመቀበል ያስቸግራል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ ያለው የነዳጅ ዋጋ እዚህ ጭማሪ ተደረገበት መባሉም በሸማቹ ላይ የሚፈጥረው ስሜት ሊጤን ይገባ ነበር፡፡

በብዙዎች እምነት ጣራ ነክቶ የነበረው የነዳጅ ዋጋ በዓለም ደረጃ ዝቅ ማለት እንዲሁም በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀውን ኢታሎን ከነዳጅ ጋር ደባልቆ ለገበያ ከቀረበ የነዳጅ ዋጋ እንዲቀንስ ምክንያት ይሆናል የሚለውንም አመለካከትና ተስፋ እንዲቀጭጭ አድርጎታል፡፡

ስለዚህ የአሁኑ የነዳጅ ጭማሪ ይዞት የሚመጣው የዋጋ ጭማሪን ሸማቹ እንዲሸከም የተፈረደበትና ቢያንስ ያለችውን ጠባብሶ ይመገብበት የነበረውን ኬሮሲን (ነጭ ጋዝ) እንኳ መንግሥት ሊደጉም አለመፍቀዱ ምን ታስቦ እንደሆነ ግራ ከማጋባቱም በላይ የነዳጅ ጭማሪውን በተመለከተ መንግሥት የወሰደውን እርምጃ መልሶ ማጤን ይኖርበታል፡፡
 
< Prev   Next >