| በኬንያ መጠለያ ካምፕ ውስጥ ግጭት ተቀሰቀሰ |
|
|
| Wednesday, 23 January 2008 | |
|
በኬንያ መጠለያ ካምፕ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት ከሰላሳ በላይ ሰዎች መሞታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ በኬንያ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች በጎሳ በመቧደን ግጭት መቀስቀሱ ተዘግቧል፡፡ የአይን ምስክሮችን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው ከቅዳሜ ጀምሮ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ የተቀሰቀሰው ግጭት በኩኩዩና በሎው ጎሳዎች መካከል መሆኑ ታውቋል፡፡ የኩኩዩ ጎሳዎች የፕሬዚዳንት ኪባኪ ወገኖች ሲሆኑ የሎው ጎሳ አባላት የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ የግጭቱ ተሳታፊዎች ጎራዴና ቀስት የታጠቁ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የአገሪቱ ፖሊስ ግጭቱን እያባባሰ ነው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡ በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት የልማት ኮሚሽነር ሊዊስ ሚኬል የተቃውሞ ሰልፈኞችን ለመበተን የኬንያ ፖሊስ ከገደብ ያለፈ ኃይል ተጠቅሟል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ሙሻራፍ በአውሮፓ ጉብኝት ጀመሩ የፓኪስታኑ ፕሬዚዳንት ፔርቬዝ ሙሻራፍ በዴሞክራሲና ሽብርተኝነትን በመከላከል ርዕሰ ጉዳይ በአውሮፓ የስምንት ቀን ጉብኝት ጀመሩ፡፡ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በብራሰልስ፣ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይና በሲውዘርላንድ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሻራፍ በጉብኝታቸው ወቅት ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ሽብርተኝነትን በመዋጋትና በዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ በፓኪስታን ከተደረገውን አወዛጋቢ የዳግም ምርጫና የቤናዚር ቡቶ ግድያ ወዲህ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው የአውሮፓ መሪዎች በቤናዚር ቡቶ ላይ ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማስተካከል ጥረት የሚያደርጉ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡ በኩባ የፓርላማ አባላት ምርጫ ተካሄደ በኩባ ያለፈው እሁድ የፓርላማ አባላት ምርጫ መካሄዱን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡ የአሜሪካ መንግስትና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምርጫውን ተቃወሙ፡፡ የሰማንያ አንድ አመት የዕድሜ ባለፀጋው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በምርጫው ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ለማድረግ ተስኗቸዋል፡፡ የካስትሮ ተቃዋሚዎችና የአሜሪካ መንግስት ምርጫን እንደማይቀበሉት ገልፀዋል፡፡ ምርጫው የሚያሳፍር ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |