Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow የባለስልጣኑ 519 አዳዲስ ረቂቅ ሰነድ አዘጋጁ
የባለስልጣኑ 519 አዳዲስ ረቂቅ ሰነድ አዘጋጁ Print E-mail
Wednesday, 23 January 2008

የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት በመንግሥት የልማት እቅድ ቅድሚያ በተሰጣቸው ዘርፎች ዙሪያ 519 አዳዲስ ደረጃዎች የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ማዘጋጀቱን አስታወ

በመንገድ ግንባታና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተዘጋጁት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ በመንገድ ሥራ ላይ የ292 የኢትዮጵያ ደረጃዎች የመጨረሻ ረቂቅ ማዘጋጀቱን፣ በኮንስትራክሽን እቃዎች የ55 ደረጃዎች ረቂቅ ሰነድ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፆ፣ በደረጃዎችና ሰርተፍኬሺን ካውንስል ከፀደቁ በኋላ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ሆነው ለዘርፎቹ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱ እምነት መኖሩን አስታውቋል፡፡

(አዲስ ዘመን ጥር 13 ቀን 2000 ዓ.)

ከአስር ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኘ

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በዘንድሮው የምርት ዘመን ከ10 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ በተያዘው የምርት ዘመን ከታረሰውና በሰብል ከተሸፈነው 200 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ከ10 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን፣ ሰብሎቹ ጤፍና ስንዴ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላና ድንች ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን፣ የአትክልትና ፍራፍሬም ምርት እንደሚገኝበት ተገል..ል፡፡

 (ዋኢማ)

 ጤፍና የተፈጨ አሸዋ ቀላቅሎ ሸጧል የተባለ ተጠርጣሪ ተያዘ

በሐረር ከተማ በ14 ኩንታል ነጭ ጤፍ ውስጥ የተፈጨ አሸዋ ቀላቅሎ ሸጧል የተባለው ተጠርጣሪ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው የተያዘው ሸዋ በር በተባለው የገበያ ስፍራ የሸጠው ጤፍ በወንፊት ሲጣራ አሸዋው ተለይቶ በመውጣቱ ነው፡፡ ተርጣሪው ኩንታሉን በ450 ብር ሂሣብ መሸጡንና ግለሰቡም በቁጥጥር ሥር ሆኖ ድርጊቱ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

(ኢዜአ)


ከ51 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የሐር ፋብሪካ ሊገነባ ነው

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የሐር ፋብሪካ 51 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ በትግራይ ክልል እንደሚገነባ የፋብሪካው ዳይሬክተር ገለፁ፡፡

የፋብሪካ ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ማምረት እንደሚጀምር የፋብሪካው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን ሁኔታ ከህንፃው ዲዛይን ጀምሮ ሀሳቡ እንዲካተት የፋብሪካው ዳይሬክተርና የኤም.ኤች ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርመው የፋብሪካው ዲዛይን ክለሳ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

(ዋኢማ)


በሙስና ወንጀል የተከሰሱ  በገንዘብ ተቀጡ

የኦሮሚያ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው ሰባት የዱከም ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች ላይ የምሥራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሁለት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና በሁለት ሺህ ብር ቅጣት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡

ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን የወሰነው በአንድ መዝገብ የተከሰሱትን አምስት ሰዎች በዱከም ከተማ አስተዳደር የጨረታ ኮሚቴ ሆነው ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት የተሰጣቸውን ስልጣን አለአግባብ በመጠቀማቸው መሆኑን የኮሚሽኑ ማስታወቂያና ቅስቀሳ ክፍል ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

(አዲስ ዘመን ጥር  ቀን 2000 ዓ.ም)

 
< Prev   Next >