Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ከኢትዮጵያውያን አይሁዶች አብዛኞቹ...
ከኢትዮጵያውያን አይሁዶች አብዛኞቹ... Print E-mail
Wednesday, 23 January 2008

ከኢትዮጵያውያን አይሁዶች አብዛኞቹ በዝቅተኛ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል

ወጣቶችን በትምህርት ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ ነው

ኢትዮጵያውያን አይሁዶችን በትምህርት ለመርዳት የተቋቋመው የእስራኤል ኢትዮጵያውያን አይሁዶች የትምህርት ተቋም ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያውያን አይሁዶች የትምህርት ሁኔታ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ትምህርታዊ ብቃት በአጠቃላይ ከእስራኤል ሕዝብ አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ሊባል እንደሚችል የአገሪቷን ትምህርት ሚኒስቴር ጠቅሶ ፣ጀሩሳሌም ፖስት፣ ዘግቧል፡፡

በቅርቡ የወጣው የትምህርት ሚኒስቴሩ አሀዝ እንደሚያመለክተው አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ በአንደኛና በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ውጤት ብቻ መካከለኛና ከመካከለኛ በላይ ነው፡፡ ሠላሳ ሁለት በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ብቻ በዓመት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት የሚያስችል ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብቁ ሲሆኑ ባለፉት አራት ዓመታት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ጉልህ የሚባል መሻሻል አለመኖሩን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

የእስራኤል ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ተቋም በእስራኤል ያሉ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ረገድ ትኩረት ሰጥቶ ከሚንቀሳቀስባቸው ጉዳዮች ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ተጨማሪ የማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፣ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በትምህርት ዙሪያ ባሉ ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል፣ ተማሪዎቹ በእስራኤል ጥሩ የሥራ እድል ባላቸው ሙያዎች እንዲሰለጥኑ ማድረግና ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከወንጀልና አደንዛዥ እፅ እንዲጠበቁ ማድረግ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የተቋሙ ራስን የማስቻል ፕሮክቶች አትራፊ ያልሆኑ የኅብረተሰብ ማኅበራትን በማደራጀት በትምህርትና በቅጥር ፖሊሲዎች ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በሚመለከት በሚወጡ ፖሊሲዎች ላይ ተጽእኖ ማሳደር እንዲችሉ አቅማቸውን ማጎልበት ዙሪያ እንደሚያጠነጥኑ የጀሩሳሌም ፖስት ዘገባ ያመለክታል፡፡ ባለፈው ዓመት ተቋሙ መረጃና ቁሳቁሶችን በመርዳት እንዲሁም አውደ ጥናቶች ሴሚናሮችን በማዘጋጀት ግጭት የመፍታት ስልቶችን የሚመለከት ሥልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡

ዘገባው እንደሚያመለክተው የእስራኤል ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ተቋም ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተቋማት በተለይም ከወጣቶችና ከተማሪዎች ጋር በጋራ ይንቀሳቀሳል፡፡ የኢትዮጵያውያን ማኅበራትን በተለይም የተማሪዎችና የወጣቶችን በገንዘብና በቁሳቁስ ይደግፋል፣ የማኅበራቱን እንቅስቃሴ ያቀናጃል፣ ፕሮጀክቶቻቸው ተግባራዊ እንዲሆኑ ድጋፍ ይሰጣል፣ የኢትዮጵያውያን አይሁዶች የትምህርትና የቅጥር ሁኔታን ለማሻሻልም የትምህርትና የቅጥር መብትን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ስለኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል፡፡

በሌላ በኩል መንግሥት ከትምህርትና ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ፖሊሲዎች የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሁኔታ ያገናዘቡ እንዲሆኑ በተለያየ መንገድ ቅስቀሳ ያካሂዳል፡፡ ይህ የሥራ ገበያውን ለኢትዮጵያውያን ምሩቃን ክፍት በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦ የሚኖረው ሲሆን ሥራ አጥነትንና ድህነትን በመቀነስ በኩልም ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን አይሁዶች በእስራኤል ከሚገጥሟቸው ችግሮች መካከል ሥራ አጥነት በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን አይሁዶችን የትምህርት ሁኔታ በሚመለከት በተለያየ መልኩ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ለማድረግ ቅስቀሳዎች ቢደረጉም በዚህ ረገድ በፖሊሲ አውጪዎች አመለካከትም ሆነ በፖሊሲዎች ላይ የታየው መሻሻል አጥጋቢ የሚባል እንዳልሆነ ጀሩሳሌም ፖስት አስታውቋል፡፡

አብዛኛው ኢትዮጵያውያን አይሁዶች በተለይም በማንኛውም ሥራ ላይ የመሰማራት አቅም ያላቸው፣ በአገሪቱ የሥራ ገበያ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን፣ በተለያየ ሥራ ላይ ከተሰማሩትም አብዛኞቹ በጉልበት ሥራ ላይ የተሰማሩና አነስተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ባችለር ዲግሪ ካላቸው ኢትዮጵያውያን አይሁዶች መካከል አብዛኞቹ ሥራ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ዘገባው ያመለክታል፡፡

የእስራኤል የኢትዮጵያውያን አይሁዶች ተቋም የኢትዮጵያውያን ምሩቃንን የቅጥር ሁኔታ ለማሻሻል በሚያደርገው እንቅስቃሴ ወቅታዊ ችግሮችን በመቅረፍ ዘላቂ መፍትሄዎች ለማምጣት ከፍትህ ተቋማት፣ ከማዘጋጃ ቤቶችና ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጋር እንዲሁም ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ይሠራል፡፡

የተቋሙ የሚዲያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በእስራኤል ሚዲያ ራሳቸውን በመወከል ችግሮቻቸውን ማንፀባረቅ የሚችሉበትን እድል ፈጥሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለያዩ የሕትመትም ሆነ የኤሌክትሮኒክ የመገናኛ ብዙሃን መሥራት የሚችሉ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በትምህርታቸው መሠረት መቀጠር የሚችሉበትን ሁኔታ አመቻችቷል፡፡ 
 
በጋዜጣው ሪፖርተር

 
< Prev   Next >