Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Thursday
Jan 08th
Home arrow Sections arrow አብዛኞቹ ሴት አሜሪካውያን...
አብዛኞቹ ሴት አሜሪካውያን... E-mail
Sunday, 26 October 2008
Imageአብዛኞቹ ሴት አሜሪካውያን ማንን እንደሚመርጡ አልወሰኑም

በቅርቡ ለሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ብዙኃኑ ሴቶች ማንን እንደሚመርጡ ከውሳኔ ላይ ስለመድረሳቸው ሴንተር ፎር አሜሪካን ውሜን ኤንድ ፖሊቲክስ የተሰኘ ተቋምን ጠቅሶ ኒው ብረንስዊክ ዘገበ፡፡

ለምርጫው የቀረው ሁለት ሳምንት የማይሞላ ቢሆንም 60 በመቶ የሚደርሱ ሴት መራጮች ድምፃቸውን ለማን እንደሚሰጡ ግልጽ ያለመሆኑን ፒው ሪሰርች ሴንተር ፎር ፒፕል ኤንድ ዘ ፕሬስ የተባለው ማዕከል ያሰባሰበው አዲስ የሕዝብ አስተያየት ሲያመለክት 61 በመቶ ነጭ መራጮች እስካሁን ከውሳኔ አልደረሱም፡፡

ሰሞኑን የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው በጠቅላላው ከተመዘገቡ መራጮች ውስጥ ስምንት በመቶው የትኛውን ተወዳዳሪ እንደሚመርጡ አልወሰኑም፡፡ አራት በመቶ አፍሪካ አሜሪካውያንና ስድስት በመቶ የሌላ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ለኦባማም ሆነ ለማኬይን ድምፅ ለመስጠት ገና ያልወሰኑ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

በሌላ በኩል በግዛቶችና በአገር አቀፍ ደረጃ የተሰባሰቡ የሕዝብ አስተያየት እንደሚያመለክቱት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ6-7 በመቶ የሚደርስ የፆታ ልዩነት ይስተዋላል፡፡ ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ ተመዝግበው ማንን እንደሚመርጡ ባልወሰኑ ወንዶችና ሴቶች መካከል ያለ የፆታ ልዩነት ነው፡፡ 
Last Updated ( Monday, 27 October 2008 )
 
< Prev   Next >