Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ሰዶ ማሳደድ
ሰዶ ማሳደድ E-mail
Wednesday, 23 January 2008

በሪፖርተር ጋዜጣ ጥር 11 ቀን 2000 እትም መጀመሪያ ገጽ "ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ንብረት እየታገደ ነው፤ የኮበለሉ ተጠርጣሪዎች ተላልፈው እንዲሰጡ ይደረጋል" በሚሉ ርዕሶች የቀረበው ዜና በብሄራዊ ባንክ ላይ የተፈፀመው ዝርፊያ የተቀነባበረና በጥቅም የተያያዙ ኃላፊዎች እጅ እንዳለበት ያሳያል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ለወርቅ ሳይሆን ለባሌስትራ ግዢ እስከ 200 ሚሊዮን ብር ማውጣት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ እጅግ ከባድ የሆነ አሻጥር እየተፈፀመ መሆኑን፤ እንዲሁም ተቆርቋሪ፣ ኃላፊነት የሚሰማውና ከሙስና የፀዳ ኃላፊ እጦት መኖሩንም ያመላክታል፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ አሻጥር የፈፀሙትን ኃይሎች በፍጥነት መብቱ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት አቅርቦ ሕጋዊ የሆነ ቅጣት ሊፈጸምባቸው ይገባል፡፡

ይህ አይነቱ እኩይ ተግባር የሀገርን አንድነት ለመናድ አውጆ ከመጣው የውጭ ጠላት አድራጎት ተለይቶ መታየት የለበትም፡፡ "ወርቁን እንዳንከፍተው እንታዘዝ ነበር" በማለት ስሙን ለመግለጽ ያልፈለገው አንድ የብሄራዊ ባንክ ሰራተኛ የሰጠው ጥቆማ ጉዳይ የኃላፊዎች እጅ እንዳለበት ያመለክታል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ክትትልና ቁጥጥር የሚባል ነገር እንደሌለ፣ ቢኖርም ለስም ያህል እንጅ በወጉና በአግባቡ የሚከናወን አለመሆኑንም ከጥቆማው መገንዘብ ይቻላል፡፡

በሀገር ሀብት ላይ እንደዚህ አይነት ከባድ ዝርፊያ ፈጽመው የኮበለሉት ተላልፈው እንዲሰጡ የሚያደርግ አካሄድ ሊኖር ይችላል፡፡ አካሄዱ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚከናወን ወይም የሚወጡት ሳይሆን እጅግ ውስብስብ ነው፡፡ ለተግባራዊነቱም ብዙ ወጪ፣ ጊዜና ድካምን ይጠይቃል፡፡ ይህም መንግሥትን ለተጨማሪ ወጪ ይዳርጋል፡፡

ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ለመዳን በአሰራር ላይ ተገቢውን የክትትልና ቁጥጥር መስመር መዘርጋት፣ እቃው ወርቅ ወይስ ሌላ ነገር መሆኑን የሚለይ አካሄድ መከተል ያስፈልጋል፡፡ ይህንን መሰረታዊ የአሰራር ሥርዓት ሳይከተሉ መንቀሳቀስ ለዝርፊያ ወይም ለሙስና በር መክፈት ይሆናል፡፡ ዝርፊያውም ከተፈፀመ በኋላ ክትትል ማድረጉ ትርፉ ሰዶ ማሳደድ ብቻ ይሆናል፡፡

(መርዕድ ከተማ፣ ከአውቶብስ ተራ)

 
< Prev   Next >