| የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ቀዳሚ... |
|
|
| Wednesday, 23 January 2008 | |
|
የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ቀዳሚ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ እንደሚሆን ተጠቆመ ለግቤ ፕሮጀክት 470 ሚሊዮን ዩሮ ይጠበቃል ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ዘጠኝ የሀይል ማመንጫዎችን በመገንባት የውጪ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ለግቤ ፕሮጀክት 470 ሚሊዮን ዩሮ እየተጠበቀ ነው፡፡ በጐረቤት አገር ያለውን ፍላጐትና የኃይል አቅርቦት እጥረት መሠረት ያደረገ እንደሆነም የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊ በመጥቀስ ሱዳን ትሪቡን ከትናንት በስቲያ ዘግቧል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የፕሮግራምና እቅድ ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ መኩሪያ ለማ እንዳብራሩት፤ የተጀመሩትና የታቀዱት የኃይል ማመንጫዎች ሲጠናቀቁ ኃይል ትልቅ የወጪ ንግድ ገቢ ማስገኛ ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ በ2011 ከአምስት የሀይል ማመንጫ ግድቦች 3"150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የታቀደ ሲሆን፣ ከ3.2 ቢሊዮን በላይ ዩሮ እንደሚፈጅ ተገምቷል፡፡ አቅሙ በ2018 ወደ 9,000 ሜጋ ዋት ለማድረስ የታቀደ ሲሆን ያለውን ተጨማሪ ኃይል ለኬንያ፣ ለጅቡቲና ለሱዳን ለመሸጥ ታስቧል፡፡ የግቤ ቁጥር አራት ፕሮጀክት ከ1.9 "ሊዮን በላይ ወጪ የሚደረግበት ሲሆን 2000 ሜጋ ዋት የሚሆን ሀይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ በግቤ ግድብ የመነሻ ጥናቱ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅና፣ ኢትዮጵያ ከአራቱ ፕሮጀክቶች ለሦስቱ ገንዘብ የምትፈልግ ሲሆን ዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድ ፌይር ፈንድ ፋውንዴሽን 470 ሚሊዮን ዩሮ ለጊቤ ነባር በሆነው ሀሌሌ ወራቤሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ እንደሚሰጡም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ የጣሊያኑ የሳሊኒ ኮስትሩቶሪ ኤስ.ፒ.ኤ ከአምስቱ ሶስቱን ግድቦችና የ1870 ሜጋ ዋት ሃይል ያለው የግቤ ቁጥር ሦስት ፕሮጀክት በመሥራት ላይ መሆኑም ተገል"ል፡፡ የአምስቱ ግድቦች ግንባታ ሲጠናቀቅ 200 ሜጋ ዋት ለጅቡቲ፣ 200 ሜጋ ዋት ለሱዳንና 500 ሜጋ ዋት ለኬንያ ለመሸጥ የሚያስችል የቅድሚያ ስምምነት ላይ መደረሱንም አመልክተዋል፡፡ በባህር ውስጥ ለውስጥ የ26 ኪሎ ሜትር የመስመር ዝርጋታ በማድረግ ለየመንና ለጅበቲ ኤሌክትሪክ ለመሸጥ መታቀዱንም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያና የኬንያ የመስመር ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት የሚያስችለውን የ196 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት የመነሻ ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |