Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የኩዌቱ ኩባንያ የምድር ባቡር...
የኩዌቱ ኩባንያ የምድር ባቡር... Print E-mail
Wednesday, 23 January 2008

የኩዌቱ ኩባንያ የምድር ባቡር አገልግሎትን ለመግዛት እየተደራደረ ነው

የኩዌቱ ፉአድ አልጋሚና ልጆቹ የተባለ ኩባንያ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አገልግሎት ለመግዛት ከኢትዮጵያና ከጅቡቲ መንግሥታት ባለስልጣናት ጋር እየተደራደረ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በሚኒስትሮች ደረጃ ሊወሰኑ ባልቻሉ ጉዳዮች ላይ ውሣኔ ለመስጠት የ15 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አምሳሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ባለፈው ሣምንት የሁለቱ አገሮች ሚኒስትሮችና የኩባንያው ኃላፊዎችን ያካተተ ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ድርድር እያደረገ ሲሆን ሚኒስትሮቹ አሁን መወሰን ባልቻሉባቸውና የፖለቲካ ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከ15 ቀን በኋላ በድጋሚ በመምከር ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ፡፡

የሁለቱ አገራት ሚኒስትሮች የጥገና ወጪውን የሁለቱ መንግሥታት እንደሚሸፍኑ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን የባንክ ብድር በሚያገኙበት ሂደት ላይም ተወያይተዋል፡፡

የሐዲዱን የጥገና ወጪ የሁለቱ አገራት መንግሥታት የሚሸፍኑ ሲሆን በቅድሚያ በመሠረተ ልማት፣ ቢሮ፣ ሐዲድና የስቴሽን ጥገና እንደሚከናወንም ገልፀዋል፡፡ ያሉትን መስመሮች በመጨመር ዙሪያ በቀጣይ ውይይት እንደሚኖር አቶ ብርሃኑ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተደረሱት ስምምነቶችና በቀጣይ በሚደረገው የውይይት ፕሮግራም በሚደረሰው ስምምነት መሠረት የመግባቢያ ሰነድ ይፈረማል፡፡

በድርድሩ ከአውስትራሊያ፣ ከአውሮፓና ከእስያ የተውጣጡ ባለሐብቶች ተሳታፊ እንደነበሩ የገለፁት አቶ ብርሃኑ፣ ድርጅቱ የተመረጠው አቅምና ልምድ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ተሞክሮው መሠረት ባቀረበው ፕሮፖዛል አማካይነት ነው፡፡

 ኩባንያው የግዮን ሆቴሎችና ሶደሬ መዝናኛ ለመግዛት ድርድር ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በቤዛዊት ሥዩም

 
< Prev   Next >