| ኢትዮጵያ በሳንባ ነቀርሳ በሽታ... |
|
| Sunday, 16 November 2008 | |
|
ኢትዮጵያ በሳንባ ነቀርሳ በሽታ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ነች
በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት በዓለም ላይ ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን በመግደል የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ዋነኛ ቀዳሚ መንስኤ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡ (ዋኢማ) ፋብሪካው በ4ዐዐ ሚሊዮን ብር ወጪ የማስፋፋት ሥራ እያካሄደ ነው በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ቢራ ፋብሪካ በ4ዐዐ ሚሊዮን ብር ወጪ የተለያዩ የማስፋፊያ ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ዋናው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ጆን ፖል ብላዜ እንዳመለከቱት በመከናወን ላይ ከሚገኙት የማስፋፊያ ተግባራት መካከል ሦስት የመጥመቂያ ጋኖችን የማስተካከል ሥራ ይገኝበታል፡፡ የማስፋፊያ ሥራዎቹ ከሁለት ወራት በኋላ ሲጠናቀቁ በአሁኑ ወቅት በዓመት የሚመረተውን 43 ሺ ሄክቶ ሊትር ቢራ ወደ 6ዐ ሺ ሄክቶ ሊትር ከፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡ (ኢዜአ) ማህበሩ ከ1 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሴት ተማሪዎች ድጋፍ እያደረገ ነው "ፍሬ አዲስ ኢትዮጵያ የሴቶች ማሕበር" 1 ሺህ 2ዐዐ ለሚሆኑ የገጠር ደሃና ወላጅ አልባ ሴት ተማሪዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ቀዳማዊት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ገለፁ፡፡ ማህበሩ የሚያበረክተውም ድጋፍ የተማሩ ሴቶችን ቁጥር ለማሳደግ፣ ሴቶች ከወንዶች እኩል የመብታቸወ ተጠቃሚና ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ለከፍተኛ አመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት ለማብቃት ነው፡፡ (ዋኢማ) ግዙፍ ፋብሪካ ሊገነባ ነው ስፔንቴክስ የተሰኘ ታዋቂ የድርና ማግ አምራች ኩባንያ ከኮምቦልቻ ከተማ 3ዐዐ ሺ ስፔንድል (እንዝርት) ያለው ግዙፍ ፋብሪካ እንደሚገነባና ይህም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ምርትና ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ማዕከል አስታወቀ፡፡ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ እንደገለፁት ድርጅቱ 5ዐ ሺ ሔክትር የጥጥ ማምረቻ መሬት ጠይቆ ተዘጋጅቶለታል፡፡ (አዲስ ዘመን) ሀገሪቱ ከ350 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች ኢትዮጵያ በ2ዐዐ1 ሩብ ዓመት ብቻ ወደ ተለያዩ አገሮች ከላከቻቸው ምርቶች 351 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የውጭ ንግድ ማስፋፊያ መምሪያ ተወካይ አስታወቁ፡፡ በሩብ ዓመቱ የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በአጠቃላይ 28 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ተወካዩ አቶ ግርማ ገለልቻ ገልፀዋል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |