| በዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ለሁለተኛ ጊዜ ሊመጡ ነው< |
|
|
| Sunday, 27 January 2008 | |
|
የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሮበርት ቢ ዞሊክ በቀጣዩ ሣምንት ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፣ ሞሪታኒያ፣ ላይቤሪያና ሞዛምቢክን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚጐበኙ ተገለፀ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በአዲስ አበባ በሚካሄደው 10ኛው የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች መደበኛ ስብሰባ እንደሚሳተፉ ተገል ል፡፡ ባንኩ ያወጣው መግለጫ እንደሚለው ጉብኝቱ በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የሚያደርገውን እገዛ ለመተካትና አጋር ድርጅቶች የሚሰጡትን እርዳታ ለማሳደግ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡ በጉብኝታቸውም በአዲስ አበባ በሚካሄደው ጉባኤ በምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች፣ በግብርና ልማትና የምግብ እህሎች ዋጋ መጨመርን ተከትሎ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጐች በመርዳት ዙሪያ ከአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እንደሚወያዩ ተገል"ል፡፡ የዓለም ባንክ የአፍሪካ ህብረት አካባቢ አገሮች ቅንጅት፣ አመራር፣ በግጭት አወጋገድ፣ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ለአህጉራቸው ልማት ተሳታፊ በሚሆኑበት ሁኔታ ላይ እንደሚሠሩ ያመለከተው ዘገባ ፕሬዚዳንቱ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ሁለቱ ተቋማት በጋር የሚሠሩበትን ሂደት እንደሚያጠናክር ታምኖበታል ብሏል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጉናክ ዲዮፍ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 10ኛው የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች መደበኛ ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ ተገል"ል፡፡ ዶክተር ዲዮፍ ተጨማሪ የ7 ቀናት የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ነገ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |