| የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ፀረ-መንግሥት... |
|
| Sunday, 27 January 2008 | |
|
የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ፀረ-መንግሥት እንቅስቃሴዎች መስፋፋታቸውን አስታወቀ የመንግሥት ተቋዋሚዎች ቀደም ሲል ሠላማዊ ወደነበሩ ስፍራዎች ሀይላቸውን በማስፋፋት በመካከለኛና በታችኛው ጁባ አካባቢ ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ የአፍሪካ ህብረት ማስጠንቀቁን ኢሪን ዘግቧል፡፡ "የሰርጐ ገቦቹ ስትራቴጂ ባላቸው አቅም ብዛት ባላቸው አካባቢዎች ሁካታ በመፍጠር የሽግግር መንግሥቱን መዳከም ነው፡፡ የሽግግር መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ቦታዎች ወታደሮችን ማሠማራት እንደማይችል ለሁሉም ግልፅ ነው" በማለት አልፋ ኦማር ኮናሬ ተናግረዋል፡፡ በማስከተልም በተለይም ከሲሊማዮ ወደብ በሚገኝ ገቢ ላይ በጐሳዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የአልሸባብ ቡድን አዳዲስ ምልምሎችን በመካከለኛውና በታችኛው አልሸባብ እያሰለጠነ ለመሆኑ ሪፖርቶች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡ የታችኛው የሸበሌ አካባቢን የጦር መሣሪያዎችን ለማስገባት እየተጠቀሙት እንደሆነና የሽግግር መንግሥቱም በተሰነዘረበት ጥቃት ይህን አካባቢ ለቅቆ ወደ ባርዶግል ለማፈግፈግ መገደዱን፣ በጠረፋማ አካባቢዎች ደግሞ በሽግግር መንግሥቱና በኢትዮጵያ ሠራዊት ይዞታ ላይ ጥቃት እያደረሱ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገል..ል፡፡ ይህ አለመረጋጋት ንፁሀን ዜጐች ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር፣ ለብዙሃን መፈናቀልና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካላት እርዳታ እንዳይደርስ ምክንያት ሆኗል፡፡ ተመድ እንዳስታወቀው ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ 240..000 የሚሆኑ ሰዎች ሞቃዲሾን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን በ2007 አጠቃላይ 600,000 የሚሆኑ ሰዎች ከተማዋን ጥለው ተሰደዋል፡፡ "በፑንት ላንድና በሶማሊላንድ ዋነኛ ክልሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ስደት ምክንያት የሆነ ሲሆን 30,000 ሰዎች በዚህ ውጊያ ምክንያት ተፈናቅለዋል" በማለት ተናግረዋል አልፋ ኦማር ኮናሬ፡፡ የሰብዓዊ ድርጅቶችንና ሠራተኞቻቸውን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች፣ ለሞቃዲሾ አፍጐይ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ የሌሎች መንገዶች መዘጋት የሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ችግር እያስከተሉ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ገለፃ፣ የሽግግር መንግሥቱ ከሰጠው ነፃ ፈቃድ ውጪ የተዘጉ መንገዶችን ለመጠቀም የሚጠየቀው ቀረጥ ከፍተኛ ሲሆን የእነዚህ ሠራተኞች ቁጥር ሦስት መቶ ሰላሳ ስድስት ደርሶ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የትራንስፖርት ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች እርዳታዎች የሚደርሱት ዘግይተው ነው፡፡ ጥቅምት 8ና 24 ላይ የተፈፀመው መድፍና የቦንብ ጥቃት እንዲሁም የዲሴምበር 19ኙ ጥቃት አፍሪካ ህብረት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መሆናቸውን ሪፖርቱ ትኩረት አድርጐበታል፡፡ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ባደረገው የሠላም ማስከበር ተልዕኮ 1600 የዩጋንዳ ሠላም አስከባሪዎችን ያሰማራ ሲሆን አፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ሊያሰማራ ያሰበው 8000 ሰራዊት ስምንት መቶ የሚሆኑትን እንደምታዋጣ የሚጠበቀው ብሩንዲ ሠራዊቶቿን ማሰማራት ጀምራለች፡፡ የሽግግር መንግሥቱና የኢትዮጵያ ሠራዊት በአገሪቱ ሠላም ለማስፈን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ሁኔታዎች በጣም አስከፊ መሆናቸውን በመጥቀስ ሞቃዲሾ ውስጥ በቀን በአማካይ ከአምስት እስከ ስድስት አደጋዎች እንደሚደርሱ ህብረቱ አሳውቋል፡፡ የእርስ በርስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ባሉት አስራ አምስት ዓመታት፣ በምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ስፖንሰርነት ኬንያ ላይ ከተደረገው የእርቅ ኮንፈረንስ ከተደረገ በኋላ በሶማሊያ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት የተደረጉ ጥረቶች ብዙም ውጤታማ ሊሆኑ አለመቻላቸውን አስታውቋል፡፡ ሶማሊያ በአስከፊ ቀውስና አለመረጋጋት ውስጥ መሆኗን፣ መሠረታዊ የሕዝብ አገልግሎቶችን ማሟላት የሚችል ውጤታማ መንግሥት አለመኖር፣ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስና የኢኮኖሚ መዝቀጥ በአገሪቱ እንዳለ ህብረቱ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |