Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የአንበጣ መንጋን ለመከላከል...
የአንበጣ መንጋን ለመከላከል... E-mail
Sunday, 27 January 2008

የአንበጣ መንጋን ለመከላከል እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ሦስት ክልሎች በሚገኙ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች የተከሰተውን የበረሃና ተዛማጅ የአፍሪካ አንበጣ መንጋ ለመከላከል የሚያስችል አንቅስቃሴ በመከናወን ላይ መሆኑን የእንስሳትና እፅዋት ጤናና ጥራት ኢንስፔክሽንና ቁጥጥር መምሪያ አስታወቀ፡፡

የአንበጣው መንጋ የተከሰተው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በኦሮሚያና በጋምቤላ ክልሎች በሚገኙ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች መሆኑንም በመምሪያው የሰብል ጥበቃ ባለሙያ ወይዘሮ አዜብ ለማ ገልፀዋል፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በልዩ ልዩ ሥፍራዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ ሲሆን፣ ተዛማጅ የአፍሪካ አንበጣ የታየው ደግሞ በጋምቤላ ክልል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኮንሶ ወረዳና በአካባቢው የታየውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለማጥፋት ከጥር 13 እስከ ጥር 15 ቀን 2ዐዐዐ ድረስ በተካሄደው እንቅስቃሴ 1065 ሊትር ኬሚካል መረጨቱንና በዚህም 1015 ሔከታር መሬት ከአንበጣ መንጋ ነፃ ለማድረግ መቻሉን ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

በቀሩት ሥፍራዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ሁኔታ ለማየትና የመድኃኒት መርጨቱንም ሥራ ለማከናወን የሚያስችል አንድ የባለሙያዎች ቡድን ከጥር 15 ቀን 2000 ጀምሮ ወደ ተጠቀሱት ሥፍራዎች መንቀሳቀሱን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት ለመምሪያው ምክትል አስተባባሪ በፀሃፊዎቻቸው በኩል መልዕክት ብናስተላልፍም ሊሳካልን አልቻለም፡፡

 
< Prev   Next >