Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ኬንያውያን ሴቶች ጆንያ እንዲለብሱ ተጠየቁ
ኬንያውያን ሴቶች ጆንያ እንዲለብሱ ተጠየቁ Print E-mail
Sunday, 27 January 2008

ኬንያውያን ሴቶች በሀገራቸው ያለው ብጥብጥ እስኪቆም ድረስ ጆንያ እንዲለብሱ ጥሪ ቀረበ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በሁለት ሴቶች አነሳሽነት የተጀመረው ይህ ተግባር እየተካሄደ ያለውን ሁከት መቃወሙን ለማሳየትና ለሀገሪቱና ለሟቾቹ ሀዘንን ለመግለፅ የሚል ዓላማ ያለው ነው፡፡

ከዚህ ሌላ ለቢቢሲ ድምፃቸውን ያሰሙት አነሳሾችና ጓደኞቻቸው ፍትህ እንዲሰፍን ለመጠየቅም ጭምር ድርጊቱን እየፈፀሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

"በኬንያ ሰላም እስኪሰፍን ድረስ እንዲህ መልበሴን እቀጥላለሁ ሌሎችም እንዲከተሉን እጠይቃለሁ፡፡ ይህ ነገር ለውጥ እስኪመጣ ይቀጥላል" ብላለች አስተባባሪዋ ለቢቢሲ፡፡ በተጨማሪም "እስከዛሬ እየታገልን ያለነው ሕገመንግሥቱ እንዲለወጥና ሥልጣን ከተወሰኑ ሰዎች እጅ እንዲወጣ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ነፃ የሆነ የፍትህ ሥርዓት ይኖረናልም" ብላለች፡፡

እንደ አስተባባሪዋ ጆንያ ለብሶ በመዘዋወር ተቃውሞን መግለፅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረግ ይሻላል፡፡ በአምላክና በሕዝቡ ፊትም ራስን ዝቅ አድርጎ ማቅረብን ያሳያል፡፡

ከዚህ ሌላ ኬንያውያን ሴቶች መሪዎችና ሕዝቡ ሁሉ ሰከን ባለመንፈስ እንዲወያዩ ለማድረግና የተፈጠረውን የጎሰኝነት መንፈስ እንዳይንሰራፍ ለማድረግ በተቃውሞው እንዲተባበሩ በአስተባባሪዎቹ ተጠይቀዋል፡፡ 

 
< Prev   Next >