| ከኢትዮጵያውያን ሴቶች ግማሾቹ... |
|
|
| Sunday, 27 January 2008 | |
|
ከኢትዮጵያውያን ሴቶች ግማሾቹ ለቤት ውስጥ ጥቃት ተጋልጠዋል ከኢትዮጵያውያን ሴቶች ግማሽ ያህሉ የተለያዩ ዓይነት የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች መሆናቸውን የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤን የጠቀሰው የአጀንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ገል ል፡፡ በዘገባው እንደተጠቆመው በህጻናትና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙት ጥቃቶች ከአካላዊ ጉዳት እስከ ሞት ያሉ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ሚኒስትር ዴኤታዋ እንደገለፁት የሚመለከታቸው ሁሉ የሀገሪቱን ግማሽ ሴቶች የሚያጠቃውን የቤት ውስጥ ጥቃት ለመከላከል ሊሰሩ ይገባል፡፡ መረጃዎችን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለውም ፆታን መሰረት አድርጎ በሀገሪቱ ከሚፈፀም ጥቃት 79 በመቶ የሚሆነው በትምህርት እጦትና በሴቶች የኢኮኖሚ ጥገኝነት ምክንያት የሚመጣ ነው፡፡ ዘገባው አክሎ እንደጠቆመው ሴቶች 81 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው ቢረጋገጥም ባህላዊ አስተሳሰብና መዋቅር ምክንያት መብቶቻቸው ሊረጋገጡላቸው አልቻሉም፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |