| ዛሬ ከሁለት ሺ በላይ... |
|
| Sunday, 27 January 2008 | |
|
ዛሬ ከሁለት ሺ በላይ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ይሰጣሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኘሮጀክት ፅህፈት ቤት በቦሌ ክፍለ ከተማ በስድስት የተለያዩ ሳይቶች ላይ ያስገነባቸውን ህንፃዎች ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ቁልፍ በዛሬው ዕለት ያስረክባል፡፡ ሥራቸው ተጠናቆ ለነዋሪዎች የሚሰጡት ኮንዶሚኒየም ቤቶች 2 ሺ 359 ሲሆኑ ነዋሪዎቹ በሚገኙበት ዛሬ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ገርጂ 5 በሚባለው ሳይት ላይ ያስመርቃል፡፡ (የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኘሮጀክት ፅህፈት ቤት ጥር 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ሞት 40 በመቶ ቀነሰ በኢትዮጵያ የህፃናት ሞት ደረጃ መቀነሱን የተባበሩት መንግሥታት ህፃናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ የ2ዐዐ8 የአውሮፓ ዓመት የሥራ ሪፖርቱን አዲስ አበባ ውስጥ ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ጠንካራና አበረበታች ስትራቴጂ በመቀነስ እ.ኤ.አ ከ199ዐ እስከ 2ዐዐ6 ባደረገችው እንቅስቃሴ የህፃናቱ ሞት 4ዐ በመቶ ቀንሳለች፡፡ (አዲስ ልሣን ጥር 14 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) የፀሐይ ብርሃንን ኃይል መጠቀም ሊጀመር ነው በኢትዮጵያውያንና በጀርመን ባለሀብቶች በጋራ የሚንቀሳቀሰው ሶላር 23 ዴቨሎኘመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ የፀሐይ ብርሃንን በኃይል ምንጭነት ለመጠቀም የሚያስችል እንስቃሴ እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡ ቴክኖሎጂው ገጠራማ አካባቢዎች በአነስተኛ ወጪ ከፀሐይ ብርሃን የኃይል አቅርቦት እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ በአገሪቱ ከብክለት የፀዳ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ማስቻሉን፣ ኩባንያው በአልጀሪያ ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ፣ አይቮሪኮስት፣ ናይጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ሞሮኮ፣ ኒጀር፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ቶጐ፣ ቱኒዚያና ኡጋንዳ እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል፡፡ (ኢዜአ) በ108 ብር የአበባ ልማት ተጀመረ በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ108 ሚሊዮን ብር ካፒታል የአበባ ልማት መጀመሩን ቢዊቲ ግሪን የአበባ እርሻ ልማት ኘሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡ ድርጅቱ የመጀመሪያ ምርቱ የሆነውን 740 ሳጥን አበባ በዚህ ወር ወደ ጀርመን በመላክ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀው፣ ከኔዘርላንድስ፣ ከጃፓንና መካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ጥያቄ የቀረበለት መሆኑን፣ ለ187 ሰዎች የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን 8ዐ በመቶ የሚሆኑ ሴቶች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ (አዲስ ዘመን ጥር 14 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) ወደ ውጭ ከተላኩ የግብርና ምርቶች ከ777 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ የግብርና ምርቶች ከ777 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ ገቢ መገኘቱን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ውጭ ንግድ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ገቢው የተገኘው ወደ ተለያዩ አገሮች ከተላከ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ የቁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦና ሌሎችም አነስተኛ የውጭ ምርቶች ነው፡፡ (ዋኢማ) |
|
| Last Updated ( Sunday, 27 January 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |