Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ...
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ... E-mail
Sunday, 27 January 2008

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአዲስ ፋብሪካ ሊተካ ነው

ከሃምሳ አራት አመታት በላይ እድሜ ያለው የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሰራ አዲስ ፋብሪካ ለመተካት የሚያስችል ስምምነት ኡታም ፋብሪቴክ ኢንተርናሽናል ከተባለ የሕንድ ኩባንያ ጋር ተደረገ፡፡

የወንጂ ሸዋ ስኳር ሥራ አስኪያጅ አቶ መካሻ ለጥይበሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ እስዳስታወቁት በአዲስ መልክ የወንጂ ስኳርን ፋብሪካ ለመገንባት በወጣው አለም አቀፍ ጨረታ መሰረት አሸናፊ የሆነው የሕንዱ ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተስማማው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡

ፋብሪካውን በአዲስ መልክ ለመገንባት በወጣው ጨረታ ከ4 በላይ ኩባንያዎች ተሳታፊ እንደነበሩ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አዲሱን ፋብሪካ ለመገንባት የሕንዱ ኩባንያ ስምምነት ላይ የደረሰው ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ ነው፡፡

አዱሱ ግንባታ የቀድሞውን ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ እንዲቆምና ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርገው መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፣ አሁን ያለውን የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ማሽነሪዎች እድሜ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ በመሆናቸው የአገልግሎት እድሜያቸው እያበቃ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ከሕንዱ ኩባንያ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት እ.ኤ.አ በኦክቶበር 2010 የፋብሪካው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቅና ሥራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አዲሱ ፋብሪካም በአመት 6250 ቶን አገዳ መፍጨት የሚያስችል አቅም ያለውና በዚህም የተፈጨ አገዳ በአመት 150 ቶን ስኳር ማምረት ይቻላል፡፡

አሁን ያሉት ሁለቱ የፋብሪካው ማሽነሪዎች ግን አመታዊ ሸንኮራ የመፍጨት አቅማቸው ከ3000 ቶን ያነሰ እንደሆነ ከአቶ መካሻ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

አዲስ የሚገነባው ፋብሪካ አሁን ካለው ፋብሪካ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑን ያስታወሱት አቶ መካሻ፣ ግንባታውም የሚካሄደው በአዲስ ቦታ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ለዚህም ፋብሪካ ግንባታ የሚሆን ከ300 ሔክታር መሬት በላይ ዶዶታ የሚባል ቦታ በመዘጋጀት ላይ ሲሆን ከቀድሞው ፋብሪካ 7 ኪሎ ሜትር አካባቢ ይርቃል፡፡

በአገልግሎት ላይ ያለውን ፋብሪካ በተመለከተ ወደፊት መንግስት ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን ሠራተኞቹ ግን ወደ አዲሱ ፋብሪካ ተሸጋግረው እንደሚሰሩም ተጠቁሟል፡፡

በእቅዱ መሠረት በ2010 የፋብሪካው ግንባታ በሚጠናቀቅበት ወቅት ከሌሎች የስኳር ፋብሪካዎች ምርቶች ጋር ተደምሮ ከአገር ውስጥ ፍጆታ በላይ ለውጭ ገበያ ሊቀርብ የሚችል ምርት እንደሚገኝም ለመረዳት ተችሏል፡፡

ለዚህ ፋብሪካ ግንባታ የሚውለውን ወጪም በሚመለከት ዋና ሥራ አስኪያጁ እንዳስረዱት፣ ግማሽ ያህሉ በመንግስት በጀተ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪውን ደግሞ ከውጭ በሚገኝ ብድር ለመሸፈን መንግስት ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡

በዳዊት ታዬ

 
< Prev   Next >