Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Jul 03rd
Home arrow Sections arrow በግብረሰዶማዊነት ላይ ህገ መንግሥታዊ...
በግብረሰዶማዊነት ላይ ህገ መንግሥታዊ... E-mail
Wednesday, 24 December 2008

በግብረሰዶማዊነት ላይ ህገ መንግሥታዊ እገዳ እንዲጣል ተጠየቀ
በጋዜጣው ሪፖርተር

የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ህግ አርቃቂዎች በግብረሰዶማዊነት ላይ እገዳ የሚጥል ህግ እንዲዘጋጅ ሰኞ እለት ጥያቄ አቀረቡ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት የሃይማኖት ሰዎች ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ ባወጡት የአቋም መግለጫ በግብረሰዶማዊነት ላይ ህገ መንግሥታዊ እገዳ እንዲጣል ጠይቀዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትንም "የሞራል ዝቅጠት የመጨረሻ ደረጃ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ግብረሰዶማዊነት በህፃናትና በወጣት ወንዶች ላይ ለሚፈፀም የወሲብ ጥቃት መንስዔ መሆኑንም የሃይማኖት መሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ አቡነ ጳውሎስ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ "ይህ ድርጊት ረግብረ ሰዶማዊነትሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመደ ነው፡፡ ይህች የመጽሀፍ ቅዱስ አገር ይህንን ድርጊት አጥብቃ ታወግዛለች፡፡ ይህንን ድርጊት የሚፈፅሙ ሰዎች እንደ እንስሳ ማሰብ የተሳናቸው ናቸው" ብለዋል፡፡

"ይህንን ባህሪ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ግብረሰዶማውያን ሊታረሙ ይገባቸዋል" ግብረሰዶማዊ የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ የስድስት ወር የእስር ቅጣት ይጣልበታል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በአገሪቱ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ህገ ወጥ ድርጊት ተደርጐ የተጠቀሰ ቢሆንም በህገ መንግሥቱ ውስጥ ግን የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

"በግብረሰዶማዊያን እንቅስቃሴ ላይ ህገ መንግሥታዊ እገዳ እንዲደረግ ፓርላማውን አበክረን እንጠይቃለን" ይላል የሃይማኖት መሪዎቹ የአቋም መግለጫ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት ብዙ የማገገሚያ ማዕከላትን እንዲገነባና የወሲብና ወሲብ ነክ ፊልሞችን በሚያሳዩ ማቴሪያሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ የሃይማኖት መሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ዩናይትድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ የተሰኘው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ኃላፊ አቶ ስዩም አንቶኒቶስ በበኩላቸው ግብረሰዶማዊ መሆን የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

"ግብረሰዶማዊነት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው ብለን አናምንም፤ ከሰው ልጅ አፈጣጠር ጋርም የሚገናኝ አይደለም፤ ምንም ዓይነት ባዮሎጂካዊ መሰረት የለውም፡፡ ድርጊቱ ተቀባይነት የለውም፤ የዘቀጠ ተግባር ነው፡፡ እያንዳንዱ የሃይማኖት መሪ ድርጊቱን የዘቀጠ ግብረ ገብነት የመጨረሻ ደረጃ መሆኑን ይናገራሉ" ብለዋል፡፡
 
< Prev   Next >