| በሙስና ልማትንና መልካም አስተዳደርን... |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
በሙስና ልማትንና መልካም አስተዳደርን ለሚያደናቅፉ ምህረት የለም በኦሮሚያ ከ60 ዳኞችና ቃዲዎች ተቀጡ መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚደረገውን ትግልና ልማትን ለማስፋፋት የሚደረገውን ሩጫ በሚያስተጓጉሉ ላይ የማያዳግም ርምጃ እንደሚወሰድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አባዱላ ገመዳ አስታወቁ፡፡ ከስልሳ በላይ ዳኞች የእግድ፣ የቅጣትና የማባረር ርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ በፖሊስና በዐቃቤ ሕግ ዙሪያም ተመሳሳይ ችግር እንዳለ ተገለፀ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የማስጠንቀቂያ አስተያየት የሰጡት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በቆየውና ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በምክር ቤቱ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ታደለ ላጊሾ ባቀረቡት ሪፖርት በጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች፣ በወረዳ ፍርድ ቤቶችና በጉቦ የሚሰሩ ዳኞችና ፕሬዚዳንቶች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ ይህም በተለያዩ ገለልተኛ ክፍሎች ተጣርቶ ተረጋግጧል፡፡ የምክር ቤቱ ምንጮቻችን እንደገለፁት ፕሬዚዳንቱ አባዱላ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ምህረት እንደሌለ አስጠንቅቀዋል፡፡ ..ምህረት የለንም.. በማለት አስረግጠው የተናገሩት መልካም አስተዳደር እንዳይሰፍንና የተጀመረው ልማት እንዲጓተት በሚያደርጉት ላይ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ምክር ቤቱ በዳኞችና በፍርድ ቤቶች ዙሪያ በከፍተኛ ደረጃ የሙስና ችግር እንዳለ፣ በዚህም ሳቢያ ህዝብ ከወረዳ እስከ ክልል ፍትህ ለማግኘት እንደሚንከራተት ተጠቁሞ በቀጣዩ የምክር ቤቱ ስብሰባ ጉዳዩ ተጣርቶ ከተወሰደው የመፍትሄ ርምጃ ጋር ይቅረብልን.. በማለት አደራ ተሰጥቶ ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት በተለያየ እርከን ላይ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ዙሪያ ማጣራት ተደርጎና የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥፋተኛ በሚባሉት ላይ ርምጃ እንዲወስድ ፕሬዚዳንቱ የዕለት ተዕለት ክትትል ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በተገኙበት ወቅት ህዝብ ጥያቄ ሲያቀርብላቸው እንደነበርም ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት በጉቦ፣ በዘመድ አዝማድና በምልጃ ሰርተዋል የተባሉ በተለያየ እርከን ላይ ያሉ ዳኞች ላይ የቀረበውን የቅጣት ውሳኔ ምክር ቤቱ አጽድቆታል፡፡ በአንዳንድ የምክር በቱ አባላት ቅጣት የተጣለባቸው ዳኞች ጉዳይ በገለልተኛ ወገን ተጣርቷል? የሚል ጥያቄ ተነስቶ እንደነበርም ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አምስት ዳኞች፣ ከዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስት ዳኞች አንድ ፕሬዚዳንት፣ 17 የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችና ፕሬዚዳንቶች፣ 3 ነኢባ /ቃዲ/ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞች ከስራ እንዲባረሩ፣ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡ 14 ዳኞች ከደረጃ ዝቅ ተደርገዋል፡፡ በደሞዝ ተቀጥተዋል፡፡ 5 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ከፕሬዚዳንትነት ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል፡፡ ከጠቅላይ ፍርድ ቤተ 7፣ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት 10 ዳኞች በዳኞች ጉባኤ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 13 የወረዳ ዳኞች በዞን ደረጃ በተቋቋመው የዳኞች ጉባኤ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ሪፖርቱን ዋቢ በማድረግ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ 25 ገጽ ሪፖርት በቀረበበት የክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት ያዳመጠው ምክር ቤቱ ክርክር አድርጓል፡፡ የምክር ቤቱ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለፁት ..ወደፊትም በጥልቀት መጥራት ያለበት ጉዳይ አለ.. በማለት በዳኞችና በፍርድ ቤቶች ዙሪያ የቀረበው ሪፖርትና የተወሰደው ርምጃ በቂ እንዳልሆነ ያስገነዘቡ አሉ፡፡ ..በፖሊስና አቃቤ ህግም ላይ ተመሳሳይ ማጣራት መደረግ አለበት.. የሚል አስተያየት ተሰንዝሯል፡፡ የፍትህ አካላቱ ራሳቸውን እየመረመሩ በመሆናቸው ወደፊት የማስተካከያ ርምጃ ይወስዳሉ የሚል አቋም እንዳላቸው እነዚሁ ክፍሎች በአሰግድ ተፈራ |
|
| Last Updated ( Tuesday, 08 January 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |