| አየር መንገድ ቁጥጥሩን ያጥብቅ |
|
|
| Wednesday, 30 January 2008 | |
|
በሪፖርተር ጋዜጣ ጥር 18 ቀን 2000 ዓ.ም “በአውሮፕላን ውስጥ ተደብቀው የሄዱት የአየር መንገድ ሠራተኞች ነበሩ” በሚል ርዕስ የቀረበው ዜና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቁጥጥር ላይ ጥያቄን ያስነሳል፡፡ የተጠናከረ የምርመራና የቁጥጥር ዘዴ የለም ወይ የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥሩ ስም፣ አድናቆትና ዝና አትርፎ ቆይቷል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ አንዱ የደህንነት ጥበቃው አስተማማኝ መሆኑ ነው፡፡ በተለይ በአፄ ኃይለሥላሴ ሥርዓት አየር መንገዱ በበረራ ላይ እንዳለ አቅጣጫውን እንዲቀይር በጠላፊዎች የተቃጣበትን ሙከራ ማክሸፉ አይዘነጋም፡፡ ይህ የሚያሳየው አየር መንገዱ እንኳንስ መሬት ሆኖ ይቅርና በበረራም ላይ እንዳለ ክትትሉና ጥበቃው ምን ያህል ጠንካራና አስተማማኝ እንደነበር ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጠሮ አለማክበር ወይም በሰዓቱ አለመገኘት ሌላው ትልቁ ችግሩ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡ በተደጋጋሚ በሰዓት አለማክበር ሲወቀስ ይሰማል፡፡ “በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ” እንዳይባል አየር መንገዱ የቁጥጥሩና የምርመራው ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ጊዜው የውድድር ስለሆነ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ (አበበ ለማ፣ ከልደታ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |