| ቅንጅት የሚባል ፖርቲ በኢትዮጵያ የለም |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
አቶ ልደቱ የጣት ምልክት ለሌላ ወገን መስጠት፤ ቅንጅትን እንደ ማጥፋት ይቆጠራል በኢትዮጵያ ቅንጅት የሚባል ፖርቲም ሆነ አባል የለም ሲሉ አቶ ልደቱ አፈያሌው አስታወቁ፡፡ የጣት ምልክት ያለ አግባብ ለአቶ ልደቱ ፖርቲ ተሰጥቷል በማለት አቶ አየለ ጫሚሶና አቶ ተመስገን ዘውዴ ቅሬታቸውን ለምርጫ ቦርድ መግለፃቸውን አስታውቀዋል፡፡ የኢዴአፖ መድህን ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ይሄን ያሉት ምርጫ ቦርድ የቅንጅትን ምልክት ለኢዴአፖ መድህን አላግባብ ሰጥቷል በሚል አቶ አየለ ጫሚሶና አቶ ተመስገን ዘውዴ ላቀረቡት ተቃውሞ መልስ እንዲሰጡ ተጠይቀው ነው፡፡ ..ለመሆኑ ቅንጅት ›K ¨Ã;$ uTKƒ ¾T>ÖÃlƒ ›„ MÅ~ ..እኔ ቅንጅት የሚባል ፖርቲ አባል ነኝ.. የሚል ካለ ይቅረብ አርማውንም በባለቤትነት ይጠይቅ ብለዋል፡፡ አያይዘውም ፕሬዚዳንቱም ሆኑ ሌሎች ቅንጅት ለሚባል ፖርቲ መዋጮ የከፈሉበትን ወይም አባል የሆኑበትን የመታወቂያ ደብተር የላቸውም ብለዋል፡፡ በምርጫ 97 አራቱ ፖርቲዎች ተጣምረው በቅንጅት ስም በሁለት የጣት ምልክት ተወዳድረው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ልደቱ፤ ..እኔም የተወዳደርኩበት ምልክት የጣት ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን በእጬነት የቀረብኩት በኢዴአፖ መድህን ደብዳቤ ነው ሌሎቹም ያደረጉት ይሄንኑ ነው፡፡ ከዚህ በተለየ መልኩ የተወዳደረ ካለ መግለጫ ይስጥ.. ቅንጅት ለምርጫ የተጠቀመበት ምልክት በባለቤትነት መጠየቅ የሚችሉት በወቅቱ ተጣምረው የነበሩት አራቱ ፖርቲዎች ናቸው፡፡ ሶስቱ ጥያቄውን አላቀረቡም እኛ ስለጠየቅን ተሰጠን፡፡ የምርጫ ቦርድ ጥፋት ምንድ ነው? የሚሉት አቶ ልደቱ ..በሌላ ፖርቲ የባለቤትነት ጥያቄ ማንሳት ለማደናገር ካልሆነ በስተቀር ሌላ ውጤት አያመጣም.. ብለዋል፡፡ ቅንጅትን እንደ ፖርቲ አቋቁሞ ህጋዊ ሰውነት ለማግኘት ሩጫ በሚደረግበት በአሁኑ ወቅት ቅንጅት ፖርቲ እንደነበር በማስመሰል ሁለት የሚጣላ አስተሳሰብ ማራመድ እንደማይጠቅም አቶ ልደቱ ገልፀዋል፡፡ ምልክቱን የወሰዱት በቅንጅት ስም በምርጫ ድምጽ ለማግኘት ነው፡፡ ህዝብንም ለማሳሳት ነው በሚል ለቀረበባቸው ውንጀላ ..እኛ ተጭበርብሮ የሚመርጥ አባልና ደጋፊ የለንም.. በማለት ውንጀላውን አጣጥለውታል፡፡ አቶ አየለ ጫሚሶና አቶ ተመስገንን በተመለከተ ከምርጫ በኋላ የመጡ እንጂ ቀደም ሲል ያልነበሩ በመሆናቸው ጥያቄውን ለማንሳትም ሆነ የምልክቱ ባለቤቶች ነን ለማለት ህጋዊ ህልውናና መብቱ የላቸውም ብለዋል፡፡ አርማና ምልክት አንድ አለመሆኑን ያብራሩት አቶ ልደቱ ..አርማ ያለው ፖርቲ ሁሉ አርማውን ምልክት ማድረግ አለበት የሚል ህግ የለም.. ብለዋል፡፡ አቶ ልደቱ ..እኛ ምልክት አድርገን የተወዳደርንበትን እነሱ አርማ አድርገው ስላስቀመጡት የእነሱ ይሆናል የሚል ህግ የለም.. ሲሉ ከሕግ አኳያም አለ ያሉትን የግንዛቤ ጉድለት አሳይተዋል፡፡ አቶ ተመስገን ዘውዴ የጣት ምልክትን ለኢዴአፖ መድህን መስጠት ..ህገ ወጥና አድሎአዊ አካሄድ ነው.. ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አቶ ተመስገን የጣት ምልክት የቅንጅት ምልክት ብቻ ሳይሆን አርማም ረየጣት ምልክት በማህተማችን ውስጥ አለሪ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በሀገሪቱ ህግ መሠረት የተቋቋመ የፖለቲካ ፖርቲን አርማ ለሌላ የፖለቲካ ፖርቲ የሚሰጥበት የህግ አግባብ የለም በማለት ከአቶ ልደቱ ጋር የሚለያዩበትን መልስ ሰጥተዋል፡፡ የጣት ምልክት ለሌላ ፖርቲ የተሰጠበትን አካሄድ እንደሚቃወሙና የህግ የበላይነት እንዲከበር በህግ የሚጠይቁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ ተመስገን የጣት ምልክትን ከሁሉ በመቅደም መጠየቃቸውን አስታውሰው ምርጫ ቦርድም የጣት ምልክት ያለበት ማህተም ፊርማ በመስጠት እውቅና እንደሰጣቸው አውስተዋል፡፡ ..አሁን መልሶ ለሌላ ቡድን/ፖርቲ የሚሰጥበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፤ አይገባም፣ ይህ ህገ ወጥነት ነው.. ሲሉ አብራርተዋል፡፡ አቶ አየለ ጫሚሶ በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ የፖርቲያችን አርማ የሆነውን ለሌላ አካል መስጠቱ ፖርቲው አይፈለግም ማለት እንደሆነ ብለዋል፡፡ አቶ አየለ ምርጫ ቦርድ የፖርቲውን አርማና ምልክት ተቀብሎና አፅድቆ መዝግቦ፤ እንደገና ለሌላ አካል መስጠቱ አጠያያቂ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በማያያዝም ..የምርጫ ምልክታችን ለሌላ አካል ከተሰጠና ምርጫ ቦርድ የፖርቲውን ህጋዊ ተጠሪ በተመለከተ የሚሰጠው ውሳኔ የፖርቲውን ህጋዊነት ወደኋላ የሚመልስ ከሆነ፤ በምርጫው ላይ የመካፈላችን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ይገባል.. ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ አካሄድ ላይም ጥያቄ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ አቶ አየለ ..ይህ አካሄድ ቅንጅት እንደቅንጅት በምርጫ ውስጥ እንዳይሳተፍ የሚያደርግ ሁኔታ ይመስላል.. በማለት ተናግረዋል፤ ..ምርጫ ቦርድ አንደኛውኑ ይህ ፖርቲ በአገሪቱ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ አንፈልግም ብሎ በግልፅ ሊያሳውቀን ይገባል.. ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በተሾመ ንቁና በአሰግድ ተፈራ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |