Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow የንብ ኢንሹራንስ ቦርድ እንዲቀጥል ተወሰነ
የንብ ኢንሹራንስ ቦርድ እንዲቀጥል ተወሰነ Print E-mail
Wednesday, 30 January 2008
በቀድሞ የንብ ኢንሹራንስ ሥራ አስኪያጅና በቦርዱ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ኩባንያው ከ20 በመቶ በላይ ድርሻ ያላቸው ባለአክስዮኖች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ አሁን በሥራ ላይ ያለው ቦርድ ሥራውን እንዲቀጥል ተወሰነ፡፡
ጥር 17 ቀን 2000 ዓ.ም በኢንሹራንስ ኩባንያው ኦዲተር በኩል ተጠርቶ የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ በቦርድና በቀድሞ ሥራ አስኪያጅ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ላይ ውሳኔ ለመስጠትና አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለመምረጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በእለቱ አንዳንድ ባለ አክስዮኖች የስነስርዓት ጥያቄ በማቅረብ የሁለተኛው አጀንዳ መንፈስ መቀየር አለበት በማለት በአጀንዳው ቅደም ተከተል መሠረት በቦርዱና በቀድሞው ሥራ አስከያጅ መካከል ባለው ችግር ቦርዱ ጥፋተኛ ከሆነ የሁለተኛው አጀንዳ ተፈፃሚ እንዲሆን ካልሆነ ግን ሌሎች አማራጮች እንዲወሰዱ የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ከዚህ ስምምነት በኋላ ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸው ተፈጠረ የተባለውን ችግር አብራርተዋል፡፡

ሆኖም በእለቱ በተካሄደው የባለአክስዮኖች ስብሰባ በቀድሞ ሥራ አስኪያጅና በቦርዱ መካከል ክርክር ተካሂዶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ተፈጠረ የተባለው ችግር ቦርዱን የሚያስጠይቅና ጥፋተኛ የሚያደርገው ባለመሆኑ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ሳያስፈልግ ቦርዱ ይቀጥል የሚል ውሳኔ እንዲሰጥ አድርጓል፡፡

በቦርዱ ከሥራ የታገዱትና በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጉዳያቸው የታየው የቀድሞ ሥራ አስኪያጅ ለጠቅላላ ጉባኤ ካቀረቧቸው አቤቱታዎች መካከል ቦርዱ ያለአግባብ በማኔጅመንቱ ሥራ ጣልቃ እንደሚገባና ለሥራ እንቅፋት እንደሆነባቸው ገልፀው እንደነበር ታውቋል፡፡

የቦርድ አባላቱም የሠራነው በእቅድ የያዝነውን ሥራ በአግባቡ መተግባሩን ማረጋገጥ ነው፡፡ በእቅዳችን መሠረት መሰራት ያለባቸውን ሥራ እየተከታተልን እናስፈጽማለን እንጂ ለሥራ እንቅፋት አልሆንም በማለት ተከራክረዋል፡፡

የቀድሞ ሥራ አስኪያጅም የተባረሩት በጥፋት መሆኑንም የቦርዱ አባላት አመልክተዋል፡፡ የሁለቱን ወገን ክርክር ያደመጠው ጠቅላላ ጉባኤ ቦርዱ ሥራውን እንዲቀጥል የሚለውን ውሳኔም ያፀናው ከ90 በመቶ ድምጽ በላይ ነው፡፡  

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >