| ክቡር ሚኒስትር |
|
|
| Wednesday, 30 January 2008 | |
|
/የአፍሪካ ሚኒስትሮች ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡ ነገ የመሪዎች ይጀመራል፡፡ ለስብሰባ የመጡት አፍሪካዊው ክቡር ሚኒስትር ከአንዱ አስተናጋጅ ኮሚቴ አባል ኢትዮጵያዊ ጋር ማምሻውን ለመዝናናት ወጥተዋል/ - ካዛንቺስ ነው የምትወስደኝ? - እንዴ ክቡር ሚኒስትር ካዛንቺስን እንዴት አወቋት? - በርግጥ በዘር ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን በተለይም አዲስ አበባን በሚገባ አውቃታለሁ፡፡ በተለይ ካዛንቺስን፡፡ - እንዴት ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ድሮ ዲያሎ ቴሌ እዚህ እያሉ ከሳቸው ጋር እሰራ ነበር፡፡ ወጣት እያለሁ፡፡ እዚህ ካዛንቺስ እየመጣሁ ነበር የምዝናናው፡፡ - እሺ እዛ እንሂድ፡፡ ይህ እኮ ነው ካዛንቺስ የሚባለው፡፡ - ጎበዝ፡፡ አየህ አሁንም ሰው እየተዝናና ነው፡፡ ዋናው የአዲስ አበባ መዝናኛ ቦታ ይኸ ነው? - አይ ክቡር ሚኒስትር፣ እርስዎ የድሮውን ነው የሚያውቁት፡፡ አሁን ስንትና ስንት ዘመናዊ ባርና ሬስቶራንት መጨፈሪያና መዝናኛ ቦታ አለ፡፡ ካዛንቺስ ድሮ ቀረ፡፡ - እኔ ፎቆችና መጠጥ አልወድም፡፡ ትንናሽ ቤቶች ሆነው ዘፈንና ሴቶች ያሉበት ቦታ ነው የምወደው፡፡ - ለዚያማ ከካዛንቺስ የበለጠ ያበደና የለየለት ሰፈር አለ፡፡ - ምን የሚሉት? - ቺቺኒያ፡፡ - ምን? - ቺቺኒያ ይባላል ክቡር ሚኒስትር፡፡ - እስቲ እዛ ውሰደኝ፡፡ ረሄዱሪ - አንተ መኪና ማቆሚያም አይገኝም፡፡ - አዬ ክቡር ሚኒስትር ያበደ ቦታ ነው ብዬዎት የለም፡፡ እንግባ? - ይኸውልህ ከአንድ ጫፍ እንጀምርና ሁሉንም እያየን በሌላው ጫፍ እንጨርሳለን፡፡ - ግን ክቡር ሚኒስትር፣ ነገ የመሪዎች ስብሰባ ስለሚጀመር እንዳይደክምዎት? - ስብሰባ ገባሁ አልገባሁ ለውጥ የለውም፡፡ የእኔ ፕሬዚዳንት በስብሰባው ከተገኙ በቂ ነው፡፡ - መጥተዋል? - የሊቢያው መሪ አብረን እንሄዳለን ስላሉዋቸው አብረው ይመጣሉ፡፡ - የግል አውሮፕላን ስለሆነ በሆነ ጊዜ መምጣት ይችላሉ፡፡ ችግር የለም፡፡ - የሊቢያው መሪ እንኳ በመኪና እንሄዳለን ነው - ከሊቢያ እስከ አዲስ አበባ? - አዎን፣ በል በል አሁን ስለ መዝናናት እናውራ ስለስራና ስብሰባ እንዳታነሳብኝ፡፡ - መዝናናት ይወዳሉ ክቡር ሚኒስትር? - በጣም፡፡ የትም ቦታ መዝናናት እወዳለሁ፡፡ ግን የት እንደምዝናና እመርጣለሁ፡፡ ለምሳሌ ጄኔቫ ቪላ አለኝ፡፡ ግን እዛ መዝናናት አልወድም፡፡ - የራስዎ ቤት ነው ጄኔቫ ያለው፣ ክቡር ሚኒስትር? - አዎን የራሴ ነው፡፡ ከአስር ዓመት በፊት የሰራሁት፡፡ - ለጄኔቫ የሚሆን ገንዘብ ብዙ መሆን አለበት? - አዎን ብዙ ገንዘብ ነው፡፡ ያኔ የዕቃ ግዥ ኃላፊ ነበርኩ፡፡ ብዙ ገንዘብ ነበር እዚያ ቦታ፡፡ - ገባኝ፣ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ኢትዮጵያውያን ጄኔቫ ቤት ያላቸው አይመስለኝም፡፡ - አሁን አሁን እየለመዳችሁት መጣችሁ እንጅ ኢትዮጵያዊያን ፈሪዎች ናችሁ፡፡ - እንዴት ፈሪዎች? - ለጦርነት እንደናንተ ደፋር የለም፡፡ ለሌላው ግን ፊሪዎች ናችሁ፡፡ - ሰው ቢያውቅስ ብሎ መፍራት አለ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - አዎን ሰው ቢያውቅስ ብላችሁ ትፈራላችሁ፡፡፡ የእናንተ ሰው ምቀኛ ነዋ፡፡ እኛ አገር እንኳን አለፈለት፤ ብሎ ደስ ነው የሚለው፡፡ - ለነገሩ እኛም እየለመድነው ነው፤ አሁን አሁን፡፡ - በል አሁን ይህ ቦታ በቃን፡፡ ሌላ ቦታ ደግሞ ውሰደኝ፡፡ ረከመስቀል አደባባይ እስከ መገናኛ፣ ከመገናኛ እስከ ቦሌና በቦሌም እንደገና እስከ መስቀል አደባባይ ያለውን መዝናኛ የተባለ ሁሉ ሲያካልሉት አመሹ፡፡ አደሩሪ - አንተ አዲስ አበባ እንዴት ተለውጣለች? ጉድ ነው፡፡ - ይህን ሁሉ ከአሁን በፊት አላዩትም ነበር፤ ክቡር ሚኒስትር? - በጭራሽ አላየሁትም፡፡ ባውቀው ኖሮ ካዛንቺስ እልህ ነበር? ባሩ፣ ሬስቱራንቱ፣ ናይት ክለቡ ሌላ ነው፡፡ - ይህን ብቻ ነው ያደነቁት ክቡር ሚኒስትር? - ልታናግረኝ ፈልገህ ነው አይደል? - ከጀመሩት ይጨርሱት እንጅ፡፡ - ሴቶቹ ደግሞ ሌላ ሆነዋል፡፡ - ሴቶቹ እንኳ ድሮም ቆንጆዎች ናቸው፡፡ - አዎን ድሮም ስናውቃቸው ቆንጆች ናቸው፡፡ ነገር ግን ቁመቱ፣ ቅባቱ፣ ልብሱ ከየት የመጣ እንደሆነ ግራ ያጋባል፡፡ ድሮኮ ከአንዲት ኢትዮጵያዊ ልጅ ወልጃለሁ፡፡ - የት አለች አሁን? - አሜሪካ ናት - ልጁሳ? - ለወላጆችዋ ሰጠችና ጠፋች፡፡ አሁን የት እንዳለ አላውቅም፡፡ - ላፈላልግልዎት? - አይ ተው አሁንማ ረዥም ጊዜ ሆነ፡፡ የልጅቷም ቤተሰብም ደስ አላላቸውም ነገሩን አልወደዱትም፡፡ - ለምን? - ኢትዮጵያውያንኮ አንድ ችግር አለባችሁ፡፡ - ምን ችግር? - አፍሪካዊያንን የምትንቁ ይመስለኛል፡፡ - ኧረ.. - ኧረ አትበል፡፡ ከአረብ ጋር ብትጋቡ፣ ከአውሮፓ አሜሪካ ኢሽያ ጋር ብትጋቡ ቅር አይላችሁም፡፡ ከጥቁር አፍሪቃዊ ግን ደስ አይላችሁም፡፡ ሃብታምም ቢሆን ትንቁታላችሁ፡፡ - አልፎ አልፎ መጥፎ ኢትዮጵያዊ አይጠፋም፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - አልፎ አልፎ ጥሩ ሰው አይጠፋም ብትለኝ ይሻለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማለቴ ነው፡፡ - እስከዚህ ድረስ ኢትዮጵያዊያንን ጠልተዋል ማለት ነው፤ ክቡር ሚኒስትር? - ጠልቼ አይደለም፡፡ አትሳሳት ኢትዮጵያዊያንን በጣም እወዳለሁ፣ አከብራለሁ ብዙ ጠንካራ ጎን አላችሁ፡፡ ለአፍሪካውያን ያላችሁ አመለካከት ግን ትምክህትና ትዕቢት አለበት፡፡ - ምናልባት ሊሆን ይችላል፡፡ - ምናልባት አይደለም፡፡ በርግጠኝነት ነው የምነግርህ፡፡ ደግሞ የምታውቁት ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ - ምንድነው እሱ ክቡር ሚኒስትር? - በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን እየቀደሙ በመሄድ ላይ እንደሆኑ የምታውቁት አይመስለኝም፡፡ - እንዴት? - ለምሳሌ እዚህ አገር ኢንተርኔት ለመክፈት ያለው ጣጣ ያሳብድሃል፡፡ በሌላ አገርኮ በቀን ትከፍታለህ፣ በሞባይል እንኳ ዜና እናገኛለን፡፡ ትናንሽ አገሮች የሚባሉት ኢትዮጵያን አልፈው ሄደዋል፡፡ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን ጣቢያ በአስርና በመቶ ነው የሚቆጠረው፡፡ እዚህ አንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያውም የመንግሥት ብቻ ነው ያለው ማለት ስሰማ ገረመኝ፡፡ አፍሪካ አገር እንዲህ አይደለም የኢትዮጵያው ይገርመኛል፡፡ ረበመሃል ክቡር ሚኒስትሩ ስልክ በሞባይላቸው ተደወለ፡፡ አነጋገሩሪ - ጎሽ፡፡ - ምን ጥሩ ዜና ሰሙ፤ ክቡር ሚኒስትር? - ፕሬዚዳንታችን አይመጡም፡፡ ፕሮግራማቸውን ሰረዙ፡፡ - ለምን? - እኔ ምን አገባኝ፡፡ እንደውም እንቅልፍ ተጫጭኖኝ ነበር፡፡ እስኪነጋ ድረስ እንዝናና ከዛ ቀኑን ሙሉ ተኝቼ እውላለሁ፡፡ /እንዳሉትም ቀኑን ሙሉ ተኝተው ዋሉ ማታ ወደ ተዘጋጀላቸው የጥሪ እራት ሄዱ፡፡ ከአቻቸው ኢትዮጵያዊ ሚኒስትር ጋር ተገናኙ/ - እንዴ እንዴ ቀኑን ሙሉ ስፈልግዎት ነበር፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ሚኒስትር ሚኒስትርን ክቡር ሚኒስትር ሲል ያስቀኛል፡፡ - በእኛ በኢትዮጵያዊያን የክብር ምልክት ነው እንጅ አያስቅም፡፡ ቀኑን ሙሉ ስፈልግዎት ነበር ማታ አመሹ መሰለኝ? - አዎን ክቡር ፕሬዚዳንቴ እንደማይመጡ ሰለነገሩኝ የሚኒስትሮች ስብሰባ ሁኔታ እንዴት ነው ብዬ ሪፖርት ስፅፍና ስልክ ነው ያደርኩት፡፡ - ስራ ላይ ነዋ ያደሩት? - ያደርኩትም የዋልኩትም ስሰራ ነው፡፡ - ገባኝ ለነገሩ ከእርስዎ ጋር የነበረው የመስተንግዶ ኮሚቴ አባልም ነግሮኝ ነበር፡፡ - ለሱማ እናንተ እንዳታስቡ ብዬ ስዝናና አመሸን በላቸው አልኩት፡፡ - እሱማ እንደዛ ነበር ያለኝ፡፡ ስንዝናና አመሸን ነበር ያለኝ፡፡ ለምንድን ነው ክቡር ፕሬዚዳንት ያልመጡት ግን? - ከጋዳፊ ጋር እመጣለሁ ብለው ነበር፡፡ ምን እንደነካቸው እንጃ? - አሁን ተዘጋጅተዋል ክቡር ሚኒስትር? - የምን መዘጋጀት? - የኮሚቴውን ሪፖርት ሊያቀርቡ፡፡ - እኔ አይደለሁምኮ የማቀርበው፡ - እርስዎ ነዎት እንጅ፡፡ - ለምንስ ያስፈልጋል፤ ጊዜ ብንቆጥብ አይሻልም? - ግድ የለም ካልተዘጋጀ ሌሎች እንዲያቀርቡት ማድረግ ይቻላል፡፡ - ፕሬዚዳንቱ ለምን አልመጡም እያለ ሰው ከሚጠይቀኝ ተደብቄ ብቀመጥ ይሻለኛል፡፡ - እሺ ይሻላል፡፡ /ተለያዩ፣ አብሯቸው ካመሸው ኢትዮጵያዊው የመስተንግዶ ኮሚቴ አባል ጋር ተገናኙ/ - ደህና ዋሉና አመሹ፤ ክቡር ሚኒስትር? - ደህና ነኝ የእናንተ አገር አይቻልም፡፡ ድቅቅ ነው ያደረገኝ ግን በደንብ ተኛሁ፡፡ - ጥሩ ነው፡፡ እንኳን ጥሩ ተኙ፡፡ - ያ ያልኩህን እንዳትረሳ፡፡ - ምን? - ብዙ ዕቃ አለ፡፡ ለመሸጥ የምንፈልገው፤ ገዥ አምጣና ኮሚሽን ታገኛለህ፡፡ - ሕገ ወጥ ከሆነ አስቸጋሪ ነው፡፡ - እኛ የፈለግነውን ብናመጣ አንፈተሽም ያመጣነው አለ፡፡ - ዊስኪ ነው፡፡ - መጠጥ አይደለም፡፡ - ወርቅ ነው? - አዎን ወርቅ ነው፡፡ - በእኛ አገርኮ በጭራሽ እንዲህ ዓይነት ሥራ አይፈቀድም፡፡ - ምን ችግር አለ? የማላውቅ መሰለህ እንዴ፡፡ ባለፈው ጊዜ ወርቅ አምጥተው ጋዳፊ ተለቆላቸው የለም ወይ? - ከስንት ግርግር በኋላ ነዋ የተለቀቀላቸው ክቡር ሚኒስትር፡፡ - አንተም ወርቁን ሽጠው አልኩ እንጅ የሚለቀቅ ከሆነ ግርግር መፍጠር ትችላለህ፡፡ - ክቡር ሚኒስትር እርስዎ ይቀልዳሉ፡፡ - በሚሊዮን እኮ ነው የሚገመተው፡፡ አንተ እስከ መቶ ሺ ብር ኮሚሽን ታገኛለህ፡፡ - እሺ ይስጡኝ፡፡ /ተሰጠው ይዞ ሄደ በነገታው ስብሰባ ሊጀመር ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ አቻቸው ጋር ተገናኙ/ - ክቡር ሚኒስትር ዛሬም ቁጭ ብለው አደሩ ወይ? - አይ በጊዜ ተኛሁ ጥሩ እረፍት ወሰድኩ፡፡ - ዛሬና ነገም አርፋለሁ፡፡ - ጎሽ አንዳንዴ ለምን ቸኩለው እንደሚሄዱ አይገባኝም፡፡ አንድ ቀን ሁለት የሚሄዱት ያናድዱኛል፡፡ - እኔ እቆያለሁ፡፡ ግን ያ የመስተንግዶ ኮሚቴ ልጅ ብፈልገው አጥቼዋለሁና ይላኩልኝ፡፡ - እሱ አንድ ችግር አጋጥሞታል፡፡ - ምን ሆነ? - ፖሊሶች አስረውታል፡፡ - ምን አደርጎ? - ያልሆነ ዕቃ በእጁ ተገኘ ብለው አስረውታል፡፡ - ሌላ ልጅ ነገ እልክልዎታለሁ፡፡ - ለነገሩ ዛሬ ልጅህ ታሟል፤ ብለው ስለደወሉልኝ ዛሬ ብሄድ ይሻለኛል፡፡ - ሁለት ቀን አርፋለሁ ብለው ምነው ሃሳብዎን በአንዴ ቀየሩ? - ወድጄ አይደለም፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |