| ወ/ት ብርቱካንና አቶ ተመስገን ቅንጅት... |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
ወ/ት ብርቱካንና አቶ ተመስገን ቅንጅት ተዋሃደ በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው ቅንጅት በአቶ ተመስገን ዘውዴ ከሚመራው ከፖርላማና ከአዲስ አበባ የምክር ቤት ተመራጮች ጋር በአንድነት ለመስራት መስማመታቸው ተሰማ፡፡ በቅርቡ ኮሚቴ ይሰይማሉ፡፡ በክልል የቅንጅት ደጋፊዎችን የማስተባበር ሥራ በፖርላማ ተመራጮች ይጀመራል፡፡ በአቶ ተመስገን ዘውዴ የሚመራው የቅንጅት የፖርላማና የአዲስ አበባ ተመራጮች በወይዘሪት ብርቱካን ከሚመራው ቅንጅት ጋር አብረው ለመስራት ያደረጉትን ስምምነት ሕጋዊ ለማድረግና በሰነድ ለማስደገፍ የጋራ ኮሚቴ እንደሚያቋቁሙ ስማቸው የጠየቁ ተናግረዋል፡፡ በቅንጅት ስም ከፖርላማ ከ60 በላይ፣ ከአዲስ አበባ 65 የሚጠጉ ተመራጮች በአቶ ተመስገን አማካይነት ብርቱካን ከሚመራው ቅንጅት ጋር ተዋህደው መስራት መጀመራቸውን በአንድነት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ በክልልና በአስተዳደር ከተሞች ቅንጅት ያልተመረጠባቸውን ጨምሮ ያሉ ደጋፊዎች በፖርላማ ተመራጮች አማካይነት የማሰባሰብና የማደራጀት ሥራ እንደሚሰራ ከምንጮቹ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፖርላማ ተመራጭ የቅንጅት አባል ..የእገሌ ቅንጅት በማለት አራትና ሦስት ቦታ እየተከፋፈለ የሚጠራው ፖርቲያችን ወደ አንድነትና አንድ መሆን እየተቃረበ ነው.. ብለዋል፡፡ ምክር ቤቶች ያሉት የቅንጅት ተመራጮች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የገለፁት እኚሁ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የቅንጅት የፖርላማ ተመራጭ ..ህዝብ ያፈረበት፣ ስሜቱ የተጎዳበት፣ አንገቱን የደፋበትና ተስፋ የቆረጠበት ጉዳይ ሁሉ በቅርቡ የሚል እምነት አለኝ.. ብለዋል፡፡ አብሮ ለመስራት ዝርዝር ጉዳዮች እየተዘጋጁ መሆኑ ታውቋል፡፡ አብሮ የተደረገው ስምምነት አስመልክቶ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አመራር ..የወደፊቱ የትግሉ አቅጣጫና ህጋዊነትን የማረጋገጡ ጉዳይ ቅድሚያ ይሰጠዋል.. ሁለቱ ወገኖች አብሮ ለመስራት ሲስማሙ ሌላውን ወገን የማግለል ዓላማ እንደሌላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በሌላ ዜና እሳቸውን ጨምሮ አራት የላዕላይ ምክር ቤት አባላት የያዙት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ከአሜሪካ ሜናፖሊ ከቅንጅት ደጋፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡ በርሳቸው የሚመራው ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ኢንጂነር ኃይሉ የቀዶ ህክምና ካካሄዱ በኋላ በደጋፊዎች ፊት ንግግር ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
|
| Last Updated ( Tuesday, 08 January 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |