| የፈረንሳይ ፍርድ ቤት... |
|
|
| Wednesday, 30 January 2008 | |
|
የፈረንሳይ ፍርድ ቤት የቻድ አጋቾች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ የፈረንሳይ ፍርድ ቤት አንድ መቶ ሦስት ህፃናትን በቻድ የማስኮብለል ወንጀል በፈፀሙት ስድስት የእርዳታ ሰራተኞች ላይ የስምንት ዓመት እስራት ፍርድ መስጠቱን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ የቻድ መንግሥት በእርዳታ ሰራተኞቹ ላይ የስምንት ዓመት እስራት ከከባድ የጉልበት ቅጣት ጋር ያስተላለፈው ውሳኔ በቻድ ቁጣ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በፈረንሳይ መንግሥት ጥያቄ የእርዳታ ሰራተኞቹ የቻድ ፍርድ ቤት የወሰነባቸውን ፍርድ በሀገራቸው እንዲያጠናቅቁ ተወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት የፈረንሳይ ፍርድ ቤት የስምንት ዓመት እስራት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በፈረንሳይ ህግ ከባድ የጉልበት ቅጣት ባለመኖሩ የቻድ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሯል፡፡ የዙ አርክ እርዳታ ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቶፎር ላቲን ህፃናቱ በዳርፉር ግጭት ወላጆቻቸውን ያጡ መሆናቸውን በመግለፅ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ “ያቀረብነውን ማስረጃ ፍርድ ቤቱ ከግንዛቤ አላስገባም፤ የፍርድ አሰጣጡ ማስረጃን ያገናዘበ አይደለም” ሲሉ ቃል አቀባዩ ቅሬታቸውን አሳውቀዋል፡፡ የፈረንሳይ የጥብቅና ባለሙያዎች የፈረንሳይ የፍትህ ተቋም የቻድን ውሳኔ መቀነስ አይችሉም፡፡ ነገር ግን የጉልበት ቅጣቱ በፈረንሳይ ህግ ውስጥ ስለሌለ ተቀንሷል በማለት አብራርተዋል፡፡ እንግሊዛዊው ባለሀብት በዝምቧቤ ፍርድ ቤት ቀረበ ኒኮላስ ቫን ሆግስትሬተን የተባለው እንግሊዛዊ ባለሀብት ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም የወሲብ ፊልሞችን በማሰራጨት ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ባለሀብቱ በዝምቧቤ ህግ የተከለከለውን በውጭ ገንዘብ የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ መፈፀሙ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ህገ ወጥ የወሲብ ፊልሞችና ፎቶግራፎችን በሰራጨት ወንጀል ተከሷል፡፡ የዝምቧቤ ፖሊስ ግለሰቡ ሀያ ሚሊዮን የዝምቧቤ ዶላር፣ ሠላሳ ሰባት ሺ የአሜሪካ ዶላር፣ ዘጠና ሁለት ሺ የደቡብ አፍሪካ ሪንድና አንድ መቶ ዘጠና የእንግሊዝ ፓውንድ እንዲሁም አንድ መቶ የቦትስዋና ፓውል ሲያዘዋውር መያዙን ገልጿል ሲል አሶሺየትድ ኘሬስ ዘግቧል፡፡ የሱዋርቶ የቀብር ስነ ስርዓት ተካሄደ የቀድሞ የኢንዶኔዢያ ኘሬዚዳንት ሱዋርቶ ያለፈው እሁድ መሞታቸውና የቀብር ስነ ስርዓቱ ያለፈው ሰኞ በብሔራዊ ስርዓት መከናወኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ኘሬዚዳንቱ ከሠላሳ ዓመታት በላይ ሀገሪቱን በመምራት ከድህነት ማላቀቃቸው ተገልጿል፡፡ በቀብር ስነ ስርዓቱ የአገሪቱ ኘሬዚዳንት ሱሲሎ በምባንግ ዩዶዬም “ሚስተር ሱዋርቶ ለሀገሪቷ ያበረከተው አስተዋፅኦ አይዘነጋም፤ ለሁላችንም አርአያ ሆኖ አልፏል” በማለት ለሱዋርቶ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የሀገራት መሪዎች፣ ዲኘሎማቶች ተገኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል የሀገሪቱ የተቃዋሚ ኃይሎች ሱዋርቶ በሥልጣን ዘመናቸው ለሰሩት ወንጀል ቅጣት ሳያገኙ በማለፋቸው መቆጨታቸውን ገልፀዋል፡፡ “ከፓል ፓትና ከሂትለር ጋር የሚመደብ ወንጀለኛ ነው” ሲል ባድማ ሱዱጃታምኮ የተባለ የተማሪዎች ንቅናቄ አባል አማርሯል፡፡ በእስያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መሪ ብራድ አዳምስ “ሱዋርቶ ለሰሩት ሰብአዊ መብት ረገጣ ከፍትህ ቅጣት አመለጡ” በማለት ኮንነዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |