| 45 ኩንታል መዳብ ወደ ውጪ... |
|
| Wednesday, 30 January 2008 | |
|
45 ኩንታል መዳብ ወደ ውጪ ሲጓጓዝ ተያዘ
ከሰሜን ጐንደር መተማ ወረዳ 45 ኩንታል መዳብ በተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ ውጭ ሀገር ሲጓዝ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ መዳቡን የጫነው መለስተኛ የጭነት ተሽከርካሪና አሽከርካሪው የተያዙ ሲሆን፣ መዳቡ በወረዳው የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎት ለማስፋፋት ለሚካሄደው ሥራ የሚውል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አዲስ አበባ ገቡ የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (ኤፍኦኤ) ዋና ዳይሬክተር ጃክ ዲዩፍ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግና በአፍሪካ ህብረት አሥረኛው የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ በኢትዮጵያ ስድስት ቀናት የሚቆዩት ዳይሬክተሩ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ለ10ኛው መሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከሚመጡ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች መሪዎች ጋር በኤፍኦኤና በአገሮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ስለሚቻልበት ጉዳይ እንደሚመካከሩ፣ በተለይ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር አገሪቱ በማካሄድ ላይ ስላለችው የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እንቅስቃሴዎችና በግብርና ፖሊሲዎች ዙሪያ፣ በሁለቱ መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ትብብር ሰፊ የሀሳብ ልውውጥ እንደሚያደርጉም ተገልጿል፡፡ (አዲስ ዘመን ጥር 2ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) ከቆዳ ከ9ዐ ሚለዮን ዶላር በላይ ተገኝቷል የኢትዮጵያ መንግሥት የቆዳውን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማጠናከር በወሰዳቸው የተለያዩ እርምጃዎች ባለፈው የበጀት ዓመት ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ የጫማ ምርቶችን ወደ ተለያዩ የአውሮፓ አገሮች መላክ መቻሏን፣ ኤክስፖርት መር ስትራቴጂ ላይ በመመስረት ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብር ማሳደግ፣ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት፣ በግሉና በህዝባዊ ዘርፉ መካከል ያለውን ተቋማዊ ኔትወርክ ማሻሻል ወዘተ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ልማት ስትራቴጂ አላማ ሊሆን እንደሚገባው ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) በሃሰተኛ የክትባት ማስረጃ ከ1ዐዐ በላይ ሰዎች ተያዙ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሀሰተኛ ክትባት ማስረጃ ወደ ውጪ አገሮች ሊሄዱ የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎችን መያዙን አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ለዓለም አቀፍ መንገደኞች በሚሰጠው ህጋዊ የክትባት የምስክር ወረቀት ላይ አዲስ የምስጢራዊ ኮድ አሠራርና የኳራንቲን ቁጥጥር መጀመሩን፣ አስመስሎ በተሰራ ሀሰተኛ የክትባት ምስክር ወረቀትና ማህተም ከአገር ሊወጡ የነበሩት የተያዙት በቦሌና በሞያሌ መውጫ በሮች በተደረገው ጥብቅ የኳራንቲን ቁጥጥር መሆኑን፣ የተያዙትን 102 ሰዎች ከጉዞአቸው በማስቀረት ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉንም አስታውቋል፡፡ (አዲስ ዘመን ጥር 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) ወደ ሱዳን የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ ሊቀር ነው አዲስ ሥራ ተፈጥሯል በሚል በተሳሳተ መረጃ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚያደርጉትን ህገ ወጥ ጉዞ ለማስቀረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አስታወቁ፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች የሚገኙባቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ለደላሎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል ሱዳን ገብተው እየተንከራተቱ መሆናቸውንና ችግሩን ለመፍታት ኤምባሲው ከሱዳን መንግሥት ጋር በመተባበር ጥረት እያደረገ መሆኑን አምባሳደሩ ገልፀዋል፡፡ (ዋኢማ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |