| ጀንበር ሳትጠልቅ ... |
|
|
| Thursday, 31 January 2008 | |
![]() ዳምጤ አብዲሳ ለሁለት ዓመታት የልብስ ንግድ በሠራበት በሾላ ገበያ ያሉ የተወሰኑ ነጋዴዎች ከቀን ገቢያቸው አንድ ሱቅ ውስጥ በማስቀመጥ ገንዘብ ይቆጥቡ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ እሱም ሀያ ሁለት አካባቢ በተለያዩ ሥራዎች ላይ መንቀሳቀስ ከጀመረ በኋላ ይህን የቁጠባ ዓይነት መልኩን ለወጥ በማድረግ ለመሥራት አሰበ፡፡ “ሾላ ገበያ ውስጥ አንድ ሱቅ እየሄድን በየእለቱ የተወሰነ ገንዘብ እናስቀምጥ ነበር፡፡ ባለሱቁ እየመዘገበ የእያንዳንዳችንን ይቀበላል፡፡ የተወሰነ ኮሚሽን ያገኛል፡፡ እኔ ደግሞ እዚህ አካባቢ ካሉ ቡቲኮች፣ ውስኪ ቤቶች፣ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን ከሚሸጡ ነጋዴዎች፣ ጫማ ጠራጊዎችና ሹፌሮች እየተዘዋወርኩ በየእለቱ የተወሰነ ገንዘብ በመቀበል የቁጠባ ሥራ መሥራት ጀመርኩ” ብሏል፡፡ ወጣት ዳምጤ በሚያሰባስበው እቁብ (ቁጠባ) ውስጥ ሰላሳ አምስት ሰዎች አሉ፡፡ ከአሥር ብር እስከ አምስት መቶ ብር በቀን የሚጥል አለ፡፡ እቁቡ የሚወጣው በየሀምሳ ቀኑ ሲሆን ዳምጤ ገንዘቡን የሚያሰባስበው በየእለቱ ከአስር ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ እቁብተኞቹ በያሉበት በመሄድ ነው፡፡ እያንዳንዱ እቁብተኛ በየሀምሳ ቀኑ ያጠራቀመው ገንዘብ የሚሰጠው ሲሆን በየቀኑ የሚሰበሰበውን ገንዘብ በማግስቱ ባንክ ያስገባል፡፡ እቁብተኞቹ ጋር የሚቀመጥ የእለቱን ገንዘብ መውሰዱን ምልክት የሚያስቀምጥበት ካርድ አለ፡፡ እሱም በራሱ ማስታወሻ ደብተር ላይ ይመዘግባል፡፡ ለሚሰጠው አጠቃላይ አገልግሎት ከአስር አንድ ኮሚሽን ያገኛል፡፡ ይህን ሥራ ከጀመረ ሁለት ዓመት ሆኖታል፡፡ መጀመሪያ ላይ እቁብተኞችን ወይም የቁጠባ አባል የሚሆኑ ሰዎችን ለማሰባሰብ፣ በገንዘብ ቁጠባው እንዲሁም በእርሱ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ተቸግሮ ነበር፡፡ በጀመረበት ወቅት ያማከራቸው በተለያየ ሥራ ላይ የተሠማሩ ጓደኞቹ ራሳቸው የቁጠባው አባል በመሆንና ሌሎችን በማስተባበር እንዳበረታቱት ያስታውሳል፡፡ የቁጠባው አባሎች አብዛኞቹ ሀያሁለት አካባቢ የሚኖሩና የሚሠሩ ሲሆን ኡራኤል አካባቢም አባሎች አሉት፡፡ እዚያው አካባቢ ማደጉ ገንዘብ የሚቆጥቡት ነጋዴዎች በእርሱ ላይ እምነት እንዲኖራቸው እንደረዳው የሚናገረው ወጣት ዳምጤ ቁጠባውን በማሰባሰብ በሚያገኘው ኮሚሽን የብረታ ብረት ወርክሾፑን ለማስፋፋት እንደቻለ አመልክቷል፡፡ በወርክሾፑ አማካኝነት በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወረ የቧንቧ ሥራ ይሠራል፡፡ በወርክሾፑ ውስጥ በቀጥታ የብረታ ብረት ሥራ ላይ ይሳተፋል፡፡ የሠራተኞቹንና የሥራውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል፡፡ “የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ሞክሬአለሁ፡፡ ይህ የቁጠባ ሥራ ግን የብረታ ብረት ወርክሾፔን በማሳደግ ከፍተኛ እገዛ አድርጐልኛል፡፡ እያንዳንዱ ቁጠባ አባልም ከሚያገኘው የእለት ገቢ ያለበት ድረስ በመሄድ የእለቱን ገንዘብ ስለምቀበል የተወሰነ ገንዘብ መቆጠብ በመቻሉ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም እነሱ የእለት ገንዘብ ለማስቀመጥ ባንክ በመሄድ የሚያባክኑት ሰዓት አይኖርም፡፡ ገንዘቡንም ሳያጠፉት በሰዓቱ በመሄድ እቀበላቸዋለሁ፡፡ አሰባስቤ በየእለቱ ባንክ አስገባለሁ” ብሏል፡፡ አንዳንዴ ሀያ አምስት ቀን ገንዘብ ቆጥቦ ገንዘቡ እስከሚወጣበት እስከ ሀምሳኛው ቀን ድረስ ለመቀጠል ያቃተውና በዚህ መሀል ደግሞ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ሥራ የገጠመው አባል የብድር አገልግሎት ያገኛል፡፡ ይህ የብድር አገልግሎት ግን ለሥራ መንቀሳቀሻ እንጂ ከዚያ ውጭ ለሌሎች እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ሠርግ ለመደገስ ወይም ለሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች አይሰጥም፡፡ ሲጀምር በአስር ብር አባል የነበሩ ቀስ በቀስ መቶ እና ከዚያም በላይ የመቆጠብ ልምድ አዳብረዋል፡፡ ዘወትር እስከ አሥር ሰዓት በብረታ ብረት ወርክሾፑ ሲሠራ ይቆይና ከዚያ በኋላ የቁጠባ አባሎች በያሉበት በመዘዋወር ገንዘብ ይሰበስባል፡፡ ይህ ገንዘብ ማሰባሰብ እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ ይቆያል (ከውስኪ ቤቶች ገንዘብ እስኪቀበል..፡፡ ገንዘብ ከሚቆጥቡት መካከል አብዛኞቹ በቀን እስከ ሀምሳ ብር የሚቆጥቡ ሲሆን እነዚህ በቀን አሥር፣ ሀያና ሠላሳ የሚቆጥቡ አባሎች በየእለቱ ይህን ብር ባንክ ሄዶ ለማስገባት ሊሰንፉ ስለሚችሉ የዚህ ዓይነቱ ቁጠባ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ዳምጤ ያምናል፡፡ ከዚህም ባሻገር ቅዳሜና እሑድ ባንክ ዝግ ስለሚሆን አባሎች ገንዘብ ቢፈልጉ ከቁጠባቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡ አንተ በቀን ኮሚሽንህ ምን ያህል ነው? “የማገኘው ከአስር አንድ ነው፡፡ የቁጠባ ገንዘቡ በየሀምሳ ቀኑ እንዲወጣ ያደረግኩትም ገንዘቡ በርከት እንዲል ለማድረግ ነው፡፡ አሁን በቀን የማገኘው መቶ አርባ ብር ነው” በማለት መልሶልናል፡፡ የቁጠባው አባሎች ሁሌም ገንዘብ ለመስጠት ዝግጁ ሆነው እንደሚጠብቁትና የዚህ ቁጠባ ዋና ጠቀሜታው ገንዘቡን በያሉበት በመሄድ መቀበሉ እንደሆነ ገል..ል፡፡ የእስከ አሁኑ የቁጠባ እንቅስቃሴ የእለት ገቢ ያላቸውን ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ ወርሀዊ ገቢ ያላቸውን የሚያሳትፍ ቁጠባ ለመጀመርም አስቧል፡፡ ከቁጠባው ጐን ለጐን ትልቅ እቁብ (አምስት መቶ ሺህ ድረስ) ለማሰባሰብ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ “በዚህ ሥራ የሚያግዘኝ ረዳት አለኝ፡፡ ትልልቅ እቁቦችን ስጀምር ቁጠባውን ለእሱ ብተውለት እሱ ደግሞ በሥሩ ሌላ ሰውን በመቅጠር የሥራ እድል ይፈጥራል” በምሕረት አስቻለው |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |