|
Sunday, 03 February 2008 |
 የካሮ ብሔረሰብ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሐመር ወረዳ ውስጥ ይገኛል፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ውስጥ የሚኖሩት የካሮ ተወላጆች ሦስት ሺህ ይደርሳሉ፡፡ በሰብል ምርት እርሻ ይተዳደራሉ፡፡
የካሮ ቋንቋ ከኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል፡፡ ..ካሮ ውሜን፣ ኦሞ ሪቨር ሪጂን፣ ኢትዮጵያ.. በሚል ርእስ በድረ ገጽ የቀረበው ጽሑፍ እንደሚጠቁመው ብሔረሰቡ ካለው ልዩ ልዩ ባህላዊ ገጽታዎች አንዱ ሴቶች ለመዋብ የሚጠቀሙባቸው ለየት ያሉ ነገሮች መኖራቸው ነው፡፡ ሴቶች በአካላቸው፣ በደረታቸው፣ በፊታቸው ላይ የሚቀቧቸው በቀለም የተጌጡ መሆናቸው ራሳቸውን የሚያስውቡበት መንገድ ነው፡፡
በተለይ በክብረ በዓላት ወቅት ጭፈራ ላይ ተውቦ ለመታየት የሚያደርጉት ጥረት አለ፡፡ ከኖራ ድንጋይ በተቀመመ ነጭ፣ ከአለት ማዕድን በሚገኝ ቢጫ ቀለም፣ በቀይና በከሰል አካላቸውን ያስውባሉ፡፡ በፀጉራቸው ላይ የላባ ጌጥ ይሰኩበታል፡፡ የፀጉር አሠራራቸውም ይለያል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር |
|
Last Updated ( Sunday, 03 February 2008 )
|