Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በአፍሪካ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብን...
በአፍሪካ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብን... E-mail
Sunday, 03 February 2008
በአፍሪካ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብን ከወባ ለማዳን ጥረት ይደረጋል

የጤናና የንግድ መሪዎች በመጪዎቹ 5 ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ ከ3 ሚሊዮን በላይ በወባ የሚሞቱ ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በስዊዘርላንድ በተካሄደ የወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ የተካፈሉት የጤናውና የንግዱ ዘርፍ መሪዎች እንደገለፁት፣ ከ3 እስከ 5 ሚሊዮን ህይወትን በመታደግ በአመት እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር አምራች ሊሆን የሚችል ጉልበት ማትረፍ ይቻላል፡፡

የወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ሪፖርት እንዳመለከተው፣ በተለይ በአፍሪካ በወባ የሚጠቁ 30 አገራት ላይ የሚደረገውን የወባ ቁጥጥርና የህክምና አገልግሎት መጠን በመጨመር በመጪዎቹ 5 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት ይቻላል፡፡

Last Updated ( Sunday, 03 February 2008 )
 
< Prev   Next >