Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት...
የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት... E-mail
Sunday, 03 February 2008
Imageየኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት 122 ሚሊዮን ብር ሰበሰበ
ከመንገደኞች አገልግሎት ከጠበቀው ገቢ 40 በመቶውን አላገኘም

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ባለፉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ 154.09 ሚሊዮን ብር  አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ 122.09 ሚሊዮን ብር በማግኘት የእቅዱ 79 በመቶ ቢያከናውንም ዋነኛ ገቢ አድርጐ ካስቀመጠው የመንገደኞች አገልግሎት ገቢ 40 በመቶ የሚሆነውን አላሳካም፡፡
የድርጅቱን የ2000 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ ክንውን የሚያመለክተው ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው በእቅዱ መሠረት ከፍተኛ የሆነ ገቢ ይገኝባቸዋል ተብለው ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች ውስጥ የደንበኞች አገልግሎት ገቢ (ፓሴንጀርስ ሰርቪስ ቼንጅ) 82.7 ሚሊዮን ብር አገኛለሁ ብሎ፣ ያገኘው ግን 49.1 ሚሊዮን ብሩን ብቻ ነው፡፡ ይህም በእቅዱና ባገኘው ገቢ መካከል ከ33.6 ሚሊዮን ብር በላይ ልዩነት እንዲታይ አድርጓል፡፡

ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ እቅዶች የነበረው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን 122.9 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑ በእቅዱና በአፈፃፀሙ መካከል ከ31.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን የገቢ ልዩነት እንዲኖረው አድርጓል፡፡ ለገቢው ማነስ በዋናነት ሊጠቀሱ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል አስራ አምስት ከሚደርሱት የገቢ ዓይነቶት ውስጥ የተወሰኑት ከእቅዱ በታች ገቢ በማስገኘታቸው ነው፡፡

በአንፃሩ ግን ከ/ላንዲንግ ቻርጅ/  36.9 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 43.9 ብር በማግኘቱ ከእቅዱ ከ6. ማሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አነስተኛ ገቢ የተገኘባቸውን አገልግሎቶች እንዲካካስ እገዛ አድርገውለታል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ከእቅድ በታች የገቢ ክንውን በተገኘባቸው የአገልግሎት ዓይነቶች ውስጥ የፓርኪንግ ቻርጅ 1.3 ሚሊዮን ብር ይገኝበታል ተብሎ 180 ሺህ ብር ፣ራን ዌይ ራላይት ቻርጅ 13.6 ሚሊዮን ብር ይገኝበታል ተብሎ 10.5 ሚሊዮን ብር ኤክስሬይ ሰርቪስ ቻርጅ 1.2 ሚሊዮን ይገኝበታል ብሎ 686 ሺህ ብር አስገኝተዋል፡፡

የወጪን በተመለከተም በስድስት ወሩ ውስጥ 98.3 ማሊዮን ብር ወጪ ለማድረግ አቅዶ ያወጣው ወጪ ግን 47.2 ሚሊዮን ካገኘው በጠቅላላው በግማሽ የበጀት ዓመቱ የትርፍ በብር (30ኀ በመቶ) ተቀንሶ 14.1 ሚሊዮን የተጣራ 33.04 ማሊዮን ብር ማግኘቱን ያሳያል፡፡ በዚሁ ሪፖርቱ የካፒታል ፕሮጀክት እቅድ አፈፃፀምን በተመለተም ሪፖርቱ በሚሸፍነው ጊዜ ውስጥ የ28 ፕሮጀክትን ሥራ በእቅድ ተይዞ እንደነበር ጠቁሞ በነበር ፕሮጀክቶች ከተካተቱት ውስጥ አንድ የሆነው የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ  ሥራ 60.75 በመቶ ብቻ መከናወኑን አመልክቷል፡፡

በተጠቀሱት ወራት የዋና መስሪያ ቤት የግንባታ አካል የሆነው የፋይናንሻል ግምገማ ውጤት ማጽደቅ፣ የውለታ ሰነድ ማዘጋጀትና መፈራረም፣ የቁፋሮና የአፈር ቆረጣ እንዲሁም የኮንክሪት ሥራዎችን የሚያጠቃል እንደነበር ይገልፃል፡፡

ሆኖም ክንውኑ 60.75 በመቶ ብቻ እንዲሆንና ለክንውኑ ማነስ ዋናው ምክንያት የሚገነባው ህንፃ በተደጋጋሚ የዲዛይን ማሻሻያ የሚያስፈልገው ሆኖ በመገኘቱና ይህንኑ ማሻሻያ አማካሪው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ እንዲሁም የግንባታ ሥራው ከተጀመረ በኋላ ሥራ ተቋራጩ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን አሟልቶ ላለመቅረብ ሥራውን በእቅዱ መሠረት ማከናወን ባለመቻሉ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከሥራ ተቋራጩና አማካሪ መሃንዲሱ ጋር ተደጋጋሚ ስብሰባ በማካሄድ ሥራው በእቅዱ መሠረት ለማስኬድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች በመሟላታቸው ሥራው በአግባቡ ይከናወናል የሚል እምነት ላይ መደረሱንም ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

ከዚህም ባሻገር አነስተኛ አፈፃፀም ታይቶባቸዋል፡፡ ከተባሉት ፕሮጀክቶች ውስጥ የአዲስ አበባ ኤርፖርት አዲሱ ተርሚናል የውስጥ መከፋፈል ካውንተርና ቡዝ ሥራ ተጨቃሽ ሲሆን የዚህ ሥራ አፈፃፀሙም 50 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ሪፖርቱ በሚሸፍነው ጊዜ ውስጥ ከቅድመ ዝግጅት  ተከላውና ማስጀመር ያሉ ሥራዎች የታቀዱ ቢሆንም ይህ እቅድ ግማሽ ያህሉ ብቻ ተከናውኗል፡፡ ለክንውኑ ማነስ በዋናነት የተጠቀሰው ለግንባታ የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች ከውጭ ተመርቶ የሚመጣ በመሆኑ እቃው ለማጓጓዣ ከተገመተው ጊዜ በላይ በመራዘሙ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በጥቅሉ የስድስት ወሩ እቅድ አፈፃፀም በመከናወን ላይ ከሚገኙ 26 ልዩ ልዩ ሥራዎች ውስጥ 16ቱ ከ85 በመቶ በላይ 3 ሥራዎች ከ60 እስከ 85 በመቶ 7 ሥራዎች ከ60 በመቶ በታች የእቅድ አፈፃፀም አሳይተዋል፡፡

የካፒታል ፕሮጀክትን በተለከተም ከ28ቱ ፕሮጀክቶች ውስጥ 17 ፕሮጀክቶች ከ90 በመቶ በላይ፣ 6 ፕሮጀክቶች ከ60 እስከ 90 በመቶ እቅዳቸውን ሲመቱ 3 ፕሮጀክቶች ከ60 በመቶ በታች መከናወናቸውን ያሳያል፡፡

የድርጅቱን እቅድን ከማስፈፀም በተመለከተ ችግሮች ሆነው የታዩት ጉዳዮች ውስጥ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ከማስፈፀም አኳያ በሥራ ተቋራጮች የሚቀርቡ ዋጋዎች የተጋነኑ መሆን፣ የአማካሪ ድርጅቶች የሚያቀርቡት የዲዛይን ሥራ በኤርፖርት አካባቢ ካላቸው ውስጥ እውቀትና ችሎታ የተነሳ በተደጋጋሚ ማሻሻያ እንዲደረግበት መደረጉ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለምህንድስና ሙያ ብቃትና ልምድ ያለው ባለሙያ ከፍተኛ እጥረት በመኖሩ ለፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡

በዳዊት ታዬ
Last Updated ( Sunday, 03 February 2008 )
 
< Prev   Next >