Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Wednesday
Oct 15th
Home arrow Sections arrow ከ360 ሚሊዮን ብር ብድር ዕቅድ በስድስት...
ከ360 ሚሊዮን ብር ብድር ዕቅድ በስድስት... E-mail
Sunday, 03 February 2008
ከ360 ሚሊዮን ብር ብድር ዕቅድ በስድስት ወር የተሰጠው 98 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሥራዎች ኤጀንሲና የአዲስ አበባ ማህበራት ማደራጃ ተበዳሪዎችን ይልካሉ በሚል ታሳቢ ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ቢዘጋጅም በእቅዱ መሠረት ሊያበድር እንዳልቻለ ተገለፀ፡፡
በ2000 የበጀት ዓመት 360 ሚሊዮን ብር ለብድር የተዘጋጀ ቢሆንም በግማሽ የበጀት ዓመቱ ውስጥ ለብድር የተሰጠው 97.7 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ወርቅነህ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት በ1999 የበጀት ዓመት 564 ሚሊዮን ብር ለማበደር እቅድ ይዞ ሊያበድር የቻለው 100 ሚሊዮን ብር እንደነበር አስታውሰው ይህም የሆነው የአዲስ አበባ የጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች ኤጀንሲና የማህበራት ማደራጃ ተበዳሪዎችን እንልካለን ብለው ባለመላካቸው እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

ዘንድሮም በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱ ተቋማት ተበዳሪ ይልካሉ በሚል ታሳቢነት 360 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን አሁንም ሁለቱ ተቋማት አንድም  ባለመላካቸው በ6 ወራት ውስጥ ለብድር የተሰጠው ገንዘብ ዝቅተኛ አድርጐታል፡፡

ተቋሙ ይህንን ያህል በጀት ለመያዝ  የነበረው ሁለቱ ተቋማት ተበዳሪ ካመጡ ብድር የለም እንዳይባል ነው እንጂ ተቋሙ  ይይዝ የነበረው በጀት ከ150 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ እንደነበርም አቶ ሲሳይ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው የበጀት ዓመት ስድስት ወራት   የተሰጠው 97.7 ሚሊዮን ብርም በተቋሙ ቅስቀሳና ጥረት የተሰጠ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ሲሳይ በስድስት ወራት ውስጥ የተሰጠው ብር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ግን በተበዳሪ ቁጥር 69.2 በመቶ እንዲሁም በብድር መጠን 131.8 በመቶ እድገት እንዳለው ያመለክታሉ፡፡

አቶ ሲሳይ ይህ   ሊያድግ የቻለውም በሚሊኒየሙ ህብረተሰቡ ለሥራ እንዲነሳሳ ቅስቀሳ በመደረጉና የብድር ተቋሙ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት  የመዋቅር ለውጥ በማድረጉ እንደሆነ የአቶ ሲሳይ ገለፃ ያመለክታል፡፡   

የተቋሙን ብድር አመላለስ በተመለከተም በታህሳስ መጨረሻ ላይ እንዲመልስ ይጠበቅ የነበረው 50 ሚሊዮን ብር እንደነበርና ከዚህ ውስጥም 48 ሚሊዮን መመለስ መቻሉ ተጠቅሷል፡፡ ተመሳሳይ በሆነ መልኩም ባሳለፍነው የበጀት ዓመት 24 ሚሊዮን ብር ይመለሳል ተብሎ 23 ሚሊዮን ብር መመለሱ የብድር አመላለስ ላይ ብዙም ችግር እንደሌለው የኃላፊው ገለፃ ያመለክታል፡፡

“በተቋሙ የሚቆጥቡ አስቀማጮችን ለማበረታታት ሲባል ከመደበኛው ባንክ ይበልጥ 4.5 በመቶ ወለድ እንከፍላለን፡፡ ታች ያለው የህብረተሰብ ባንክ ሄዶ አይቆጥብም እዚህ ይመጣል፡፡ እኛም ለማበረታት እንጂ 4.5 በመቶ መክፈላችን የሚያዋጣ ሆኖ አይደለም፡፡”  ተናግረዋል፡፡

ባንክ የአስቀማጮች 4 በመቶ ወለድ ነው የሚሰጠው፡፡ የሚያበድረውም ህብረተሰቡ የሚፈልገው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ነው፡፡ እንደኛ አነስተኛ ብድሮችን ግን አንድ ሺህ ብር ነው፡፡ የእኛ ደግሞ ማይክሮ ፋይናንሶች አሁን ባለው ሁኔታ እስከ 24 በመቶ የሚያበድሩ አሉ፡፡.. ያሉት አቶ ሲሳይ ሁሉም ማይክሮ ፋይናንሶች ከ12 በመቶ በላይ ነው የሚያበድሩት፡፡ የእኛ ደግሞ 9 በመቶ ነው፡፡ ይህ አነስተኛ የወለድ መጠን ነው፡፡ “9 በመቶ እያበደሩ በማይክሮ ፋይናንስ አቅም አይችልም፤ መጥፋት ነው፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ አስተዳደር እኔ ጥቂት ድጋፍ አደርጋለሁ ስላለ ብቻ ከአስር ወደ ዘጠኝ በመቶ ወርደን እያበደርን ነው” ብለዋል አቶ ሲሳይ፡፡

በዚህ የወለድ መጠን ማበደሩ ተቋሙ አደጋ ላይ እንዳለ የሚቆጠር መሆኑን የሚገልፁት አቶ ሲሳይ በቅርቡ በተጠና ጥናት ብድር በአግባቡ ያበድር ከተባለ 17 በመቶ ወለድ መከፈል እንዳለበት ያመለክታል፡፡ ስለሆነም የተቋቋመው የዘጠኝ በመቶ ወለድ አነስተኛ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ አያይዘውም ይህ ተቋም እንዲኖር በአግባቡ ከተፈለገ ወለዱ ማደግ ነበረበት የሚል እምነት አላቸው፡፡

አቶ ሲሳይ አክለውም “ይህ ተቋም ጠፍቶ ደግሞ የብድር አገልግሎት ይጠፋል፡፡ ስለዚህ 17 በመቶ ካደረግን አደጋ ስለሚገጥመው ከባንክ ብድር ለማምጣት ህብረተሰቡ (የአዲስ አበባ አስተዳደር ለምሳሌ) ዋስ ይሆነናል፡፡ ዘጠኝ በመቶ ለሚሠራ ከባድ አይደለም፡፡ ለማይሠራ ግን ሊከብድ ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ብር ሠጥተን በዓመቱ 109 ብር ነው የምንቀበለው፡፡ ስለዚህ አነስተኛ ወለድ ነው፡፡

የእኛ አገልግሎት ከባንክ ጋር መነፃፀር የሌለበት ሌላው ምክንያት ባንክ ለምሳሌ 1 ሚሊዮን ብር የሚያበድረው ለአንድ ሰው ነው፡፡ እኛ አንድ ሚሊዮን ብር ለአንድ ሺህ ሰው እንሰጣለን፡፡” በማለት አቶ ሲሳይ ገልፀዋል፡፡

በቤዛዊት ሥዩም
 
< Prev   Next >