Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Wednesday
Oct 15th
Home arrow Sections arrow የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም አስከባሪ ኃይል...
የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም አስከባሪ ኃይል... E-mail
Sunday, 03 February 2008
የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም አስከባሪ ኃይል ቆይታ ለስድስት ወር ተራዘመ

የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን በኢትዮ ኤርትራ ድንበር የሰፈረው የሰላም አስከባሪ ኃይል ለአንድ ወር ያህል ጊዜ ብቻ እንዲቆይ ቢጠይቁም የሰላም አስከባሪው ቆይታ ለድስት ወር እንዲራዘም የፀጥታው ምክር ቤት ወስኗል፡፡
የሰላም አስከባሪው ኃይል ቆይታ ለአንድ ወር ጊዜ ያህል ብቻ እንዲራዘም ባንኪሙን የጠየቁት ኤርትራ የወሰደችው የነዳጅ አቅርቦት ማቋረጥ እርምጃ የሰላም አስከባሪውን እንቅስቃሴ ሽባ ያደረገው በመሆኑ ጦሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊለቅ ይችላል በሚል ምክንያት ነው፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት ዲፕሎማቶች ግን የሰላም አስከባሪው ጦር ከአካባቢው መውጣት ሁኔታው ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያመራ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ባንኪሙን ለፀጥታው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት ኤርትራ የወሰደችው የነዳጅ ማቋረጥ እርምጃ የሰላም ልዑኩ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዳይወጣ እንቀፋት ፈጥሮበታል፡፡

የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን እንደሚሉት ኤርትራ በወሰደችው የነዳጅ አቅርቦት ማቋረጥ ምክንያት የሰላም አስከባሪው ኃይል በአካባቢው ሲያደርገው የነበረውን እንቅስቃሴ ቀንሶታል፡፡

ረቡዕ ዕለት የወጣው የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ የኤርትራ መንግስት በአስቸኳይ ለአንሚ ነዳጅ ማቅረቡን እንዲጀምር ወይም ደግሞ ያለምንም ገደብ አንሚ ከውጭ ነዳጅ እንዲያስመጣ እንዲፈቀድለት አሳስቧል፡፡

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ዲፕሎማት ሁኔታውን በማስመልከት ለሮይተርስ ሲናገሩ “ኤርትራ በወሰደችው እርምጃ ምክንያት የፀጥታው ምክር ቤት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንደማይሄድ የተነዘብን ይመስለኛል፡፡ አንሚ በአካባቢው መኖሩ ሁለቱ ወገኖች (ኢትዮጵያና ኤርትራ) ወደ ግጭቱ እንዳይመለሱ ይከላከላል የሚል እምነት አለን” ብለዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች በአስር ሺ የሚቆጠሩ ሠራዊታቸውን ወደ ድንበሩ ያስጠጉ ሲሆን የፀጥታው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያና ኤርትራ በአወዛጋቢው ድንበር ያሰፈሩትን ጦር እንዲቀንሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኤርትራ መንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑት ተስፋዓለም ስዩም ማክሰኞ እለት ለፀጥታው ምክር ቤት በፃፉት ደብዳቤ መቀመጫውን ዘሄግ ያደረገው የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ለአወዛጋቢው ድንበር ጉዳይ እልባት መስጠቱን ገልፀዋል፡፡ የፀጥታው ምክር ቤቱ አሁን ትኩረት ሰጥቶ ሊከታተለው የሚገባው ጉዳይም ኢትዮጵያ ሊዓላዊ የሆነችውን የኤርትራን መሬት በኃይል ተቆጣጥራ መቀጠሏን መሆን እንዳለበት ጉዳይ አስፈፃሚው አስገንዝበዋል፡፡ ኤርትራ ስለወሰደችው የነዳጅ አቅርቦት ማቋረጥ እርምጃ ግን ያሉት ነገር የለም፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >